የአሜሪካ ሰኔት በትግይ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ማሳለፉ ተሰማ

0
255

የአሜሪካ ሰኔት በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ አስመልክቶ በትላንተናው ዕለት በነበረው ጉባኤ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ውሳኔው የተላፈው ለፊደራል መንግሰት፤ ለህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ አና በጦርነቱ እየተሳተፉ ላሉ ኃይሎች በሙሉ ነው ተብሏል።

ሁሉም በትግራይ ክልል ያሉ ሃይሎች ተኩስ እንዲያቆሙ ፤ በክልሉ የሰብአዊ መብት ጥበቃው እንዲጠናከር ፣ በትግራይ ክልል የትኛዉም ለእርዳታ ድርጅቶች የተዘጋው መንገድ ክፍት እንዲሆን እና በትግራይ ክልል የተፈፀሙት ግፎች በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ሲል የአሜሪካ ሰኔት ወሳኔ ሳልፏል።

ሴኔቱ በተደጋጋሚ የኤርርተራና የአማራ ሀይሎች እንዲውጡ ፤ የሰብአዊ ድጋፎች እንዲጠናከሩና ተኩስ አቁም እንዲፈፀም እንዲሁም ገለልተኛ ቡድን ግፎችን እንዲያጣራ ቢጠይቅም በኢትዮጵያ መንግሰት በኩል ግን ሙሉ በመሉ ተቀባይነት አላገኘም።

የኢትዮጵያ መንግሰት በገለልተኛ አካል ለማጣራት በሩን ክፍት እንዳደረገ ፤ የኤርትራ ሀይሎች እንዲወጡ መስማማቱን እና የሰብአዊ እርዳታ በሮችን ክፍት እንዳደረገ ያሳወቀ ሲሆን በአንፃሩ የተኩስ አቁም ጥሪውን ግን አልተቀበለም።

ከኢትዮጵያ ሀይሎች በተጨማሪ በትግራይ ጦርነት እየተሳተፉ ያሉት የህወሓትና የኤርትራ ሀይሎችም የተኩስ አቁሙ ጥሪው በተመለከተ ያሉት ነገር የለም።

አውሎ ሚድያ ግንቦት 12 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ