የትግራይ ሁኔታ “እጅግ አስከፊ ነው” ሲሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሐኖም ተናገሩ

0
133

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሐኖም በትግራይ ያለው ሁኔታ እጅግ አስከፊ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን ያሉት በትላንትናው እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው፡፡

በተደጋጋሚ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በኩል ለህወሓት እያገዙ ነው የሚል ትችት የሚቀርብባቸው ዶ/ር ቴዎድሮስ የትግራይ ህዝብ አሁን ያለበት ሁኔታ ለመግለፅ የምጠቀምበት ቃልም ካለ “እጅግ አስከፊ ነው በሚል ቃል ነው ልገልፀው የምችለው ብዋል፡፡

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሐኖም ከኢትዮጵያ መንግስት ለህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህውሓት) ትደግፋለክ በሚል ለሚቀርብባቸው ክስ ለማንም የወታደራዊ ሃይል ምንም እንደ ማይደግፉ ሲገልጹ መቆየታቸው ቆይተዋል።

በትግራይ ብዙ ሰው በርሃብ እየሞቱ ነው ፤ 4.5 ሚሊዮን ህዝብ የሰብአዊ ድጋፍ ያስፈልገዋል ብለዋል። በተጨማሪም ዋና ዳይሬክተሩ 91 ፐርሰንት የሚሆነው ህዝብ በክልሉ ምግብ ያስፈልገዋል። ስደት መኖሩን ያነሩት ዶክተር ቴዎድሮስ ከ 60 ሺ በላይ ሰዎች ወደ ሱዳን ተሰደዋል ብለዋል።

የሴቶች መደፈርና ዘርን መሰረት ያረጉ የጅምላ ግድያዎች በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ነው ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

የትግራይ ህዝብ ካለበት ወቅታዊ ችግር አንፃር ስለ ኮሮና ቫይረስ መጨነቅ አቁሟል ያሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ በክልሉ በኮሮና ከሚሞት ሰው በበለጠ አሁን ባለው ሁኔታ የሚሞተው ሰለሚበዛ ህዝቡ ስለኮሮና ደንታ የለውም ብለዋል።

ጨምረውም ዜጎች በክልሉ የህክምና አገልግሎትም በተገቢው ሁኔታ ማግኘት አይችሉም ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡

አውሎ ሚድያ ግንቦት 10 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ