በአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ኮሚቴ ተቋቋመ

0
53

በአዲስ አበባ ከተማ በምርጫው ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ኮሚቴ ተቋቁሟል።

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ግልጸኝነት የሰፈነበት ሆኖ እንዲጠናቀቅ ብልፅግና ፓርቲን ጨምሮ ሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች ችግሮችን የሚፈቱበት የጋራ ኮሚቴ በከተማ ደረጃ በትላንትናው ዕለት መቋቋሙ ነው የተጠቆመው።

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ እጅጉ በጋራ ኮሚቴ ምሥረታው እንደገለጹት፣ ምርጫው ለሀገራችን ምሳሌ የሚሆን እና ለሕዝቡ ተስፋ የሚሰንቅ እንዲሆን ብልፅግና ቁርጠኛ አቋም ይዞ እየተንቀሳቀሰ ነው።

በምርጫው ሂደት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ ለምርጫ ቦርድ ለማቅረብ እና ፓርቲዎች መፍታት የሚችሏቸውንም ደግሞ እንዲፈቱ ኮሚቴው መቋቋሙ ተገቢ መሆኑን አቶ ዓለማየሁ አብራርተዋል።

የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች በበኩላቸው የሀገር ሰላም እና የከተማዋ ሰላም ሁሉንም የሚመለከት በመሆኑ በፀጥታ ጉዳዮች እና በምርጫው ሂደት ላይ የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የሕዝብ አደረጃጀት ኃላፊ አቶ ሽሰማ ገ/ሥላሴ፣ ብልፅግና ፓርቲ እንደማንኛውም ፓርቲ በምርጫ ሥነ-ምግባሩ ተገዥ መሆኑን እና የአባላት የምርጫ ሥነ-ምግባር መመሪያም አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ኮሚቴ ፓርቲዎቹ በቀጣይ ቋሚ ግንኙነት የሚያመቻቹ አባላት ከተለያዩ ፓርቲዎች መምረጣቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

አውሎ ሚድያ ግንቦት 10 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ