የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የሃሰት ክስ ነው – ዘሪሁን አበበ

0
56

“የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው›› በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲፕሎማት፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ኮሚቴ አባል አቶ  ዘሪሁን አበበ ተናግረዋል፡፡

አቶ ዘሪሁን እንደገለፁት ከሆነ ግድቡ የውሃ ድርሻዬን በመቀነስ ከፍተኛ ችግር ይደርስብኛል› የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው።

የጩኸት አጠቃላይ ዓላማ ‹‹ኢትዮጵያ ለምን የዓባይን ውሃ ትጠቀማለች›› ከሚል ምቀኝነት የመነጨ ነው ያሉት አቶ ዘሪሁን፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሃይል ማመንጪያ ግድብ ነው።ውሃ ይይዛል፣ ተርባይኖቹን ይመታል፤ ኤሌክትሪክ አመንጭቶ የፍሰቱ ሂደቱን ይቀጥላል ብለዋል።

የግብጽ አካሄድ በአጠቃላይ የአባይ ውሃ ለእኛ ይገባል ከሚል የስግብግብነት መንፈስ የመነጨ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም። የዓባይን ውሃ የሚጋሩት 11 አገራት ናቸው፤ ውሃውም ለአገራቱ የሚበቃ በመሆኑ በትብብር እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ሊጠቀሙበት ይገባል ብለዋል።

ግብጽ ከግድቡ ጋር በተያያዘ የውሃ እጥረት ያጋጥመኛል የሚለው ስሞታ ፈጽሞ ሃሰት ነው ሲሉ ከአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

ግብጽ በከፍተኛ ደረጃ ውሃ ከሚያባክኑ አገራት መካከል የምትመደብ ነች ያሉት አቶ ዘሪሁን፤ ግብጽ ከፍተኛ ውሃ የሚፈልጉና በበረሃ እንዲመረቱ የማይመከሩ እንደ ሩዝ፣ ሸንኮራ አገዳ፣ ጥጥና የመሳሰሉት ሰብሎችን እንደምታመርት ጠቁመዋል።

በአውሮፓ ገበያ ከግብጽ የመጣ እንጆሪ፣ ቃሪያና ሩዝ ይታያል። ይሄ የሚመከር አይደለም።

ማምረቻው ብቻ ሳይሆን ውሃውን የሚያመርቱበት መንገድ በከፍተኛ ደረጃ እንደጥንት ፈርኦኖች ውሃውን ለከፍተኛ ትነት በሚያጋልጥ መልኩ መሆኑን አመልክተዋል።

የሙቀቱ መጠኑ እጅግ በጣም ከፍተኛ በሆነና በተንጣለለ ሜዳ መገንባቱ ውሃውን በከፍተኛ ደረጃ ለትነት እንደሚያጋልጠው አመልክተው፤ በግድብ ምክንያት ከ15 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውሃ በትነት ይባክናል ብለዋል። ሂደቱ በብረት ድስት ውሃ እንደማፍላት እንደሚቆጠርም ጠቁመዋል።

አውሎ ሚድያ ግንቦት 09 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ