ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከካናዳ አምባሳደር ስቴፋን ጆቢን ጋር ተወያዩ

0
145

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የካናዳ አምባሳደር ሆነው አዲስ የተሸሙት በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

በቅርቡ የተሸሙት አዲሱ አምባሳደር በኢትዮጵያ ከሚገኙ የሃይማኖት አባቶች እና መሪዎች ጋር ትውውቅ ማድረጋቸውን በመጥቀስ ቅዱስነታቸው በጽሕፈት ቤታቸው ስለተቀበሏቸው ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በዕለቱ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የበላይ ኃላፊ፣ የድሬዳዋና ጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ከካናዳ ኤምባሲ ካውንስለር የሆኑት ትውልደ ሩዋንዳዊት ክብርት ማሪይ ንይራማና ተገኝተዋል፡፡

አምባሳደሩ እንደተናገሩት የካናዳ መንግሥት በኢትዮጵያ በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ተሳትፎ እንደሚያደርግ በኢትዮጵያና በካናዳ መካከልም ቆየ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዳለ በመግለጽ በተለይም ቀደም ሲል ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቸው በፊት በራሽያ ሲሠሩ ከራሽያ ኦርቶዶከስ ቤተ ክርስቲያን ጋር ተቀራርበው በመሥራት ጠንካራ ግነኙነት መመሥረት መቻላቸውን በማውሳት ይኽንኑ ተመሳሳይ ግንኑነት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር ለማጠናከር ፍላጎታቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም አምባሳደሩ ወደኢትዮጵያ ከመጡ ገና አንድ ወር እንደሆናቸው፣ ስለኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክና ትውፊት ለማወቅ ፍላጎት እንዳላቸው፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ በጣም ጥንታዊና አንጋፋ እንደመሆኗ በዓለም የታወቀች፣ በርካታ አስተዋጽኦዎችን ለሰው ልጆች እንዳበረከተች በልዩ ልዩ መንገድ ቢሰሙም አሁን በሀገሪቱ በሚኖራቸው ቆይታ የበለጠ ለማወቅ መልካም አጋጣሚ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በበኩላቸው አምባሳደሩ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ጋር ትውውቅ ለማድረግና ጠንካራ ግንኙነት ለመመሥረት ላደረጉት ጥረት ምስጋናና በማቅረብ ኢትዮጵያውያን አሁኑ ጊዜ በሁሉም የዓለም ክፍል እንደሚኖሩ፣ በሰሜን አሜሪካ አህጉር በዩናይትድ ስቴትስ እና በካናዳ መኖር ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ የኦርቶዶከስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት መሥርተው በአሁኑ ጊዜ በዩናይተድ ስቴትስ ዐሥር በካናዳ ደግሞ ሦስት የአበው ሊቃነ ጳጳሳት መንበሮች ዉም አህጉረ ሰብከት እንዳሉ በማስታወስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና በካናዳ መካከል ያለው ግንኙነት መጠናከር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም አምባሳደሩ በኢትዮጵያ በቅርቡ የሚደረገው ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ እንደሚሆን ሀገሪቱም የተረጋጋ ሁኔታ እንዲገጥማት ያላቸውን ልባዊ ምኞት በመግለጽ ውይይታቸውን አጠናቀዋል ሲል ኢኦተቤ ቴቪ ዘግቧል፡፡

አውሎ ሚድያ ግንቦት 09 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ