የኤ/ ኦ/ ተ/ ቤተ-ክርስቲያን ከ7 ዓመታት በኋላ ፓትርያርክ ተሾመላት

0
118

በኢሳያስ አፈወረቂ አገዛዝ ስር የምትማቅቀው ኤርትራ በአንባገነኑ ስርዓት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሳይኖራት ለሰባት አመታት ቆይታለች።

ነገር ግን ከአራተኛው ፓትርያርክ ሞት ከሰባት አመታት በኋላ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አዲስ ፓትርያርክ ሰይማለች።

ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን 5ኛው ፓትርያርክ በመሆን በትላንተናው ዕለት ተሰይመዋል።

በኤርትራ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሥርዓትና ደንብ መሰረት የፓትርያርኩ ዘመነ ፕትርክና የሚጀመረው በመጪው ሰኔ 6 ቀን 2013 በዓለ ሲመታቸው በአስመራ ቅድስት ማርያም ካቴድራል ከተፈፀመ በኋላ ይሆናል።

የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን 4ተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዲዮስቆሮስ በ2007 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ እስከ አሁን ያለ ፓትርያርክ ቆይታለች ።

3ተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ እንጦንዮስ በ1998 ዓ/ም በቅዱስ ሲኖዶሱ “በሃይማኖት ህፀፅ ምክንያት ተወግዘዋል” የተባለ ቢሆንም አሁን በቁም እስር ላይ ይገኛሉ።

ታዲያ አቡነ ቄርሎስ 5ኛ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ፓትራሪክ ሁኖ መመረጣቸው የማስታወቅያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል።

ኤስ ቢ ኤስ ትግርኛ በድረገፁ እንዳስነበበው ከሆነ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ባላቸው የእድሜ ፀጋ በእንባ ታጅቦ “ስልጣኑን መቀበል አልችልም” እንኳን ቢሉ የቅዱስ ሲኖደሱ ኮሚቴ በአንድ በመሆን ሲለምናቸው በትህና እሺ ብሎ ወደ መራጮች ጉባኤ ቀርበዋል፡፡

ከ81 መራጮች 63 በአካል ሲመርጡ አስሩ መራጮች ኢንተርኔት በመጠቀም ነው የመረጡት ስምቶቹ ምርጫው ላይ እንዳልተሳተፉ ነው የተገለፀው፡፡

በተጨማሪም እጩ ሆነው የቀረቡት አምስት ጳጳሳትም ፓትርያርክ ሆነው ለመሾም፣ ለመወዳደር ፈቃደኛ እንዳልነበሩ ነው የተገለጸው፡፡

አውሎ ሚድያ ግንቦት 06 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ