የቻይና ጦር ሀይል ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት እና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

0
114

የቻይና ጦር ሃይል ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት መድኃኒትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

በድጋፍ ርክክቡ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታን ጨምሮ የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ እንዲሁም ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተገኝተዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሩ የቻይና መንግስት ከሀገር መከላከያ ጋር በተለያዩ ዘርፎች ላይ በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው፣ በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት በኢትዮጵያ ዙሪያ ባደረገው ስብሰባ ቻይና ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም ላሳየችው ቁርጠኝነት አመስግነዋል።

አምባሳደሩ የቻይናና ኢትዮጵያ ወታደራዊ ግንኙነት በተለያዩ መስኮች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ይህም በሁለቱ ሀገራት አመራሮች የተፈረመው የስትራቴጂክ ግንኙነት አንዱ አካል እንደሆነ መናገራቸውን ከመከላያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

አውሎ ሚድያ ግንቦት 06 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ