የቻይናው ሲኖፋርም ክትባት የዓለም ጤና ድርጅት ይሁንታውን ሰጠ

0
84

በቻይና መንግሥት በሚተዳደረው ሲኖፋርም ኩባንያ የተመረተው የኮቪድ ክትባት ለአስቸኳይ ጊዜ ጥቅም ላይ እንዲውል የዓለም ጤና ድርጅት ይሁንታውን ሰጠ።

በድርጅት ይሁንታ ያገኘ ከምዕራባውያን ውጭ የተሠራ የመጀመሪያ ክትባት ሆኗል፡፡

ፈቃድ ከማግኘቱም በፊት ክትባቱ በቻይና እና በሌሎች አካባቢዎች ለሚሊዮን ሰዎች ተሰጥቷል፡፡

የፋይዘር፣ የአስትራዜኔካ፣ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን እና ሞደርና ክትባቶች ቀደም ብለው ከዓለም የጤና ድርጅት ዕውቅና አግኝተዋል፡፡

የተለያዩ ሀገራት ግን ቀደም ሲል በተናጠል ለአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት እንዲውሉ የቻይናውያን ክትባቶችን ፈቅደዋል፡፡

ቀደም ሲል አነስተኛ መረጃ የተለያዩ ብቻ መለቀቁን ተከትሎ የቻይና ክትባቶች ውጤታማነት አልታወቀም ነበር፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት አርብ ዕለት የሲኖፋርም ክትባትን “ደህንነት፣ ውጤታማነት እና ጥራት” አረጋግጧል ብሏል፡፡

የክትባቱ ፈቃድ ማግኘት “የጤና ሠራተኞችን እና ለአደጋ የተጋለጡ ዜጎችን ለመከላከል የሚያስፈልገውን የኮቪድ-19 ክትባት ተደራሽነት የማፋጠን አቅም አለው” ብሏል ድርጅቱ።

ክትባቱ ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች በሁለት ዙር እንዲሰጥ ይመክራል፡፡

ሌላኛው ቻይና ሠራሽ ክትባት ሲኖቫክ በሚቀጥሉት ቀናት ውሳኔ ያገኛል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የሩሲያ ስፑትኒክም በግምገማ ላይ ይገኛል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 30 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ