በትግራይ ክልል እየተፈፀመ ያለው “አረመኒያዊ ተግባር” ነው – አቡነ ማትያስ

0
422

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ብፁእ ወ ቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ በትግራይ ክልል እየተፈፀመ ያላው “አረመናያዊ ተግባር” ነው በሚል ኮነኑት፡፡

ይህንን ለመናገር ብዙ ግዜ ሞክረዉ አንደተከለከሉና  የሚያዘጋጅዋቸዉ ዝግጅቶች ሳይቀር እንዳስቀሩባቸዉ የተናገሩት አቡነ ማትያስ አሁን ያሉበት ሁኔታ ከባድ እንደሆነ ገልፀዋል “አሁን ያለሁበት ሁኔታ ራሴ ነኘ የማውቀው”  ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

ፓትሪያሪኩ ይህንን ያሉት ትላንት በአለማቀፍ ደረጃ ተቀድቶ በወጣው የ 14 ደቂቃ የቪድዮ መልእክታቸው ነው፡፡

በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፣ በሸዋሮቢት በሌሎችም ቦታዎች ችግር አለ ያሉ ሲሆን የትግራይ ግን ከሁሉም ይበልጣል ብለዋል፡፡  የትግራይ ጥቃት  ጭካኔ የተሞላበት ነው ብለዋል።

አቡነ ማትያስ “የትግራይ ህዝብ ለማጥፋት ይፈልጋሉ በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለምን እንደፈለጉ ግልፅ አይደለም” ሲሉ ተቀርፆ በተላለፈው መልእክት ይገልፃሉ፡፡

በትግራይ ክልል አብያተ ክርስትያናት ሆን ተብለዉ እንዲወድሙ ተደርጓል፤ ጅምላዊ ግድያ፤ ዘረፋና ርሃብ እየተፈጸመ ነዉ ብለዋል ፓትሪያሪኩ፡፡

“በትግራይ ክልል የተደረገው ነገር ለመቃወም ብዙ ሞክሪያለዉ ፤ ይሁን እንጂ የተናገርኳቸዉ ንግግሮች ታፍነዉ እንዲቀሩ ተደርገዋል” ብለዋል አቡነ ማትያስ፡፡

“የትግራይ ችግር እጅግ የከፋ ነው፤ ጭካኔ የተሞላበት  የአረመኔ ስራ እንደሆነ እንኳንስ እኔ አለም ያውቀዋል፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ይህንን ተከተሎ ሚያዝያ 7 ቀን 2013 ያደረኩት ቃለ ምልልስ ታግዶ ቀርተዋል ነው ያሉት ፓትራሪኩ፡፡

“በትግራይ ህዝብ እየተፈፀመ ያለው እልቂት እጅግ እስነዋሪ ነው፤ በተለይም በየቤታቸው ሲቪሎች ተገድለዉ  በስርአት ሳይቀበሩ ወደ ገደል ተወርውረዋል፡፡” በማለት የተሰማቸዉን ሀዘን ገልጸዋል፡፡

አሁንም ይህ ቪድዮ ይድረስ አይድረስ እርግጠኛ ባልሆንም ዜጎች እኔ ዝም እንዳላልኩኝና በትግራይ ክልል የተፈጸሙ አጸያፊ ተግባራት እንደማወግዝ ሰዉ እንዲያቅልኝ እፈልጋለሁ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

አቡነ ማትያስ እድል አግኝተዉ ወደ ዉጭ ሀገር ሄደዉ እንደሌላዉ ሰዉ ቢያወሩና የተሰማቸዉን ሀዘን መግለጽ እንደሚፈልጉ ተናግረዉ ይሁን እንጂ አሁን በሀገሪቷ ያለዉ ሁኔታ መናገር የሚያስችል እንዳልሆነና ለመናገር አቅምም እንዳጡ ገልጸዋል፡፡

የአለም አብያ ክርስትያናትና የአለም ተቋማት ይህንን አፀያፌ ድርጊትን ተመልክቶ ሞት፤ ግፍ እንግልት በዜጎች ላይ  የሚቆምበት ሂደቶች ላ እርዳታ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ቅድስ ፓትራሪኩ የሴቶች መደፈር የረከሰ፣ቆሻሻና አጸያፊ ተግባር መሆኑንና ድርጊቱን የሚፈጽሙ ሰዎች እጅግ እንዳሳዘንዋቸዉ እና ተግባሩን እንደሚያወግዙ ነው የተናገሩት፡፡

የገዳማት ውድመትንና የአባቶችን ስቃይ ያነሱት አቡነ ማትያስ የወልድባ ገዳም አባቶች እድሜ ልካቸው የኖሩበትን ገዳም ጥለዉ ወጥተዉ መንገድ ላይ እንዲወድቁ ማደረጉ እንዳሳዘናቸዉ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል እየተፈፀመ ያለው በደል በገበሬው ላይ ጭምር እንደሆነ ያነሱት አቡነ ማጥያስ ገበሬው ንብረቱ ተዘርፎ እንዳያርስ በርሃብ እንዲሞት መደረጉ ከዛም አልፎ የትግራይ ህዝብ ዘሩ ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ እየተደረገ ያለዉን ተግባር ኮንነዋል፡፡

ሰዎች እምንታቸው ንብረታቸው ለመጠበቅ በአኩሱም ፅዮን ማርያም ተረሽነዉ እንደቅጠል መርገፋቸዉ ፤ የባህታዊው ዘወንጊል ገዳም መመታት፤ ደብረ ዳሞ ገዳም በከባድ መሳርያ ተመቶ አባቶች መሞታቸዉ እንዳሳዘናቸዉ በቪድዮዉ ገልጸዋል፡፡

ፓትራሪኩ አክለዉም  የትግራይ ተወላጆች ፅናት፤ ጥንካሬ እንዲኖራቸው እና ወደ እግዛብሄር እንዲለምኑ ጥሪ እቅርበዋል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 30 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ