ግድቡ የሱዳንን ግማሽ ህዝብ ደህንነት አደጋ ላይ ይጥላል በማለት የሱዳኑ ሚኒስትር ያሲር አባስ መናገራቸው ተሰማ

0
190
DCIM100MEDIADJI_0644.JPG

ሱዳን የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የሱዳን ግማሽ ህዝብ ደህንነት አደጋ ላይ ይጥላል ብላለች ሲል ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

የመስኖና የውሃ ሀብት ሚኒስትሩ ያሲር አባስ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ግድቡ የሱዳንን ህዝብ የሚጎዳና ነው ማለታቸው ተሰምቷል።

በተጨማሪም ሚኒስትሩ ለመገናኛ ብዙሃን በግድቡ ዙሪያ ለተነሳው አለመግባባት መፍትሄ ለመድረስ የፖለቲካ ፍላጎት አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል፡፡

ሚኒስትሩ እንዳሉት ከሆነ ኢትዮጵያ በግድቡ ዙርያ መግባባት ላይ እንድንደርስ አትፈልግም ብለዋል፡፡

ሱዳን በግድቡ ዙርያ መስማማት እንደምትፈልግ ገልፆ ኢትዮጵያ የመጀመርያ የግድቡ ሙሌት ካከናወነች በኋላ የውሃው መጠን ቀንሶብናል ብለዋል። ሚኒስተሩ ይህንንየ ይበሉ እንጁ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ዙር ከሞላች በኋላ ሱዳን በአባይ ወንዝ ጎርፍ መጥለቅለቋና መጎዳቷ ይታወሳል።

የአባይ ውሃ መጠን መቀነሱ በቡሉ ናይል ዳርቻዎች ለሚነሩ ግማሽ ያህሉን የሱዳን ህዝብ ድህንነት አደጋ ላይ እንደሚጥል አሳሰበዋል ያሉት ፕሮፌስ አባስ ከአመት በፊት ግድቡ ውሃ ስላልተሞላ የሱዳን አርሶ አደሮች ተጎዱብን በማለት ግደቡ ጠቃሚ ነው ብለው ነበር።

የግድቡ ደህንነቱ የተጠበቀ አሠራርን ለማረጋገጥ አገራቸው የመረጃ ልውውጥን የማቀላጠፍ ስምምነት እንደምትፈልግ የተናገሩት ሚኒስትሩ ፣ ዓባይን የሚጋሩ አገሮች የመረጃ ልውውጥ መብት እንዳላቸው ጭምር ነው የገለፁት ፡፡

ነግር ግን የሱዳን ባለስልጠኖቹ በተደጋጋሚ ሀሳባቸውን እየቀያየሩ ቢሆንም ኢትዮጵያ መረጃ ለመለዋወጥ ሱዳን ባለሙያዎችን እንድትልክ ጥሪ አቅርባ ሱዳን ግን ባለሙያዎችን ከመላክ ተቆጥባለች።

ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ባላት ድንበር አቅራቢያ የ 5 ቢሊዮን ዶላር ግድብ በመገንባት ላይ ትገኛለች፤ ሀገሪቷ የምትፈልገውን የኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢኮኖሚ እድሳት ያደርግላታል

ግብፅ እና ሱዳን የናይል ውሃ ተደራሽነታቸውን ይገድባል እያሉ ለአመታት ቢከራከሩም በተጨባጭ ማስረጃና በባለ ሞያ ተጠንቶ ግን ይህ አፉርሽ ሆኖባቸዋል።

በተጨማሪም የግድቡ የውሃ ማጠራቀሚያ ምን ያህል በፍጥነት እንደሚሞላ ያልተፈታ ጉዳይ አለ ፣ ይህም የተፋሰሱ አገራት የአባይ ውሃ ተደራሽነታቸውን የበለጠ በመቀነስ እና የኃይል ማመንጫቸውን በግድቦቻቸው እንዲቀንስ አድርጓል፡፡

ኢትዮጵያ በበኩልዋ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙርያ ከሱዳንና ከብግጽ መስማማት እንደምትፈልግ ስትገልፅ ቆይታለች ይሁንጂ ሱዳንና ግብፅ ጉዳዩ ወደ አውሮፓ ህብረትና አሜሪካ ተመርቶ በዛ እንወያይ የሚል አቋም ሰይዙ ኢትዮጵያ በወገንዋ የአፍሪካ ችግር በአፍሪካ መፈታት ስላለበት ወደ አፍሪካ ህብረት መመራት እንዳለበት የሚል አቋም ነው የያዛቸው፡፡

ሶስቱ ሃገራት ስምምነት ላይ ባለደረሱበት ኢትዮጰያ በያዘችው ጊዜ የግድቡ ሁለተኛ ሙሌት እንደምታከናውን በመግለፅዋ ግብፅና ሱዳን አስቆጥተዋል፡፡

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ትላንት በቪድዮ ኮነፈረንስ ከ ሲ ኤን ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ የሶስቱ ሃገራት ጥቅሞች እውን ለማድረግ እና የተፋሰሱ አገራት በግድቡ የተለቀቀውን ውሃ እንዲጠቀሙ ለማስቻል አስገዳጅ ስምምነት ያስፈልጋል ብለዋል ፡፡

አሁን ካልተስማማን ኢትዮጵያ ግድቡ ዛሬ ልትከፍተው ነገ ልትዘጋው ትችላለች ፤ በኢትዮጵያ እጅ ላይ ነው የምንወደወቀው ፤ ለዚህም ነው በአለም አቀፍ ህግ አስገዳጅ ስምምነት እንዲደረግ የምንጠይቀው ሲሉ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ሓምዶክ የገለፁት፡፡

ኢትዮጵያ በግድቡም ሆነ በአባይ ውሃላይ አሳሪና ጠርናፊ ሰምምምነት አልፈፅምም በማለት አቋሟን ታስረዳለች።

ይህ እንዲህ እንዳለ ሱዳን ቤንሻንጉል ጉሙዝ የእኔ ነው፤ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ተቋማት እከሳለሁ ማለቷ ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዲና ሙፈቲ ማክስኞ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ አስነዋሪ ነው ሲሉ ነው የገለፁት፡፡

ሱዳን የእኔ ነው ያለችው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉዳይ ከድንበርም ሆነ ከህዳሴ ግድቡ ጋር አይገናኝም ያሉት አምሳደር ዲና የኢትዮጵያ አቋም ከተመድ ምስረታና ከሊግ ኦፍኔሽን ጅማሮ ጀምሮ የሚታወቅና ለአለም ከፍተኛ ውለታ ያለው መሆንና በእነዚህ ተቋማት ኢትዮጵያ የነበራትን ሚና ማስታወስ ያስፈልጋል ብለዋል።

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 29 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ