የፊቼ ጨምበላላ በዓል በሲዳማ ክልል እየተከበረ ነው

0
188

የዘንድሮ  የፊቼ ጨምበላላ በዓል ከ ወትሮው በተለየ  ሁኔታ  በበዓሉ  በጋራ  ከሚከናወኑ ትውፊቶች ወጣ ብሎ የኮቪድ 19 ፕሮቶኮልን በጠበቀ መንገድ እየተከበረ  እንደሚገኝ የሲዳማ ክልል ባህልና ስፓርት ቢሮ ዋና ሃላፊ አቶ ጃጎ አገኘው ለ ኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

እንደወትሮ ለበዓሉ ድምቀት የሆኑት  እንደ ቄጠላና የመሳሰሉ ባህላዊ ጨዋታዎችም በጉዱማሌ አደባባይ እንደማይኖር ተነግሯል።

ይህንንም ታላላቅ የሃገር ሽማግሌዎች  እና አባቶች በመምከር እና በመነጋገር ወረርሽኙ ሊያስከትለው የሚችለውን ጉዳት በመረዳት ህዝባዊ በሆነ መንገድ ሳይሆን ቤተሰባዊ አብሮነትን በጠበቀ መንገድ ቢከበር የተሻለ መሆኑን በመረዳት እንደተደረገ አቶ ጃጎ ነግረውናል።

ይሁን እንጂ ይህ አከባበር በየተቋማቱ፣በየወረዳውና በየቀበሌው እንደሚከበር ነው  ሃላፊው የተናገሩት ።

እያንዳንዱ የበዓሉ አክባሪም ክብረ በዓሉን በየቤቱ  ያክብር ሲባል እያንዳንዱ  ቤተሰብ ከወዳጅ ዘመዱ ጋር በጥንቃቄ በመሰባሰብ ቤተሰባዊ አብሮነትን በመፍጠር፣ቤቱ ደጃፍ ላይ እርጥብ እንጨት ወይንም “ሁሉቃ “በመትከል የዚህንም ምሳሌ በሆነው በአንድነት  በመሻገር ማክበር በመተሳስብ ማክበር  እንደሚገባ አስታውቀዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በቅርስነት የመዘገበው ይህ በዓል ዛሬ መከበር  የጀመረ ሲሆን ለተከታታይ  ሁለት ሳምንታትም እየተከበረ እንደሚቀጥል ታውቀዋል።

ፊቼ ጫምባላላ መከበር ከጀመረ ከ1800 ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን የአገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ። በዓሉ የሲዳማ ሕዝብ ማንነቱን ከተረዳበት ጊዜ አንስቶ ሲከበር ቆይቷል።

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 29 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ