የምስራቅ አፍሪካ ልዩ ልዑክ ፌልትንማን ከኤርትራ ፕሬዜዳንት ጋር ተወያዩ

0
335

በጁፍሪ ፌልትማን የሚመራው የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ ከፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በትላንትናው ዕለት ተወያዩ፡፡

የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈረወርቂ ልዩ ልዑክን ተቀብለው ለ4:00 ሰዓት ገደማ ተወያይተዋል፡፡

ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ከአሜሪካ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን እንዳስረዱ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ የማነ ገ/መስቀል በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል።

አምባሳደር ፌልማን በበኩላቸው በአፍሪካ ቀንድ እየታዩ ባሉ ችግሮች ዙሪያ የአሜሪካ አስተዳደር ያለውን አመለካከትና እይታ ለፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እንዳብራሩላቸው የኤርትራው ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ገልፀዋል።

የ62 አመቱ ጄፍሪ ፌልትማን የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ሆነው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን ሲሾሙ በምስራቅ አፍሪካ ያለው አለመረጋጋት በተለይም በትግራይ ክልል ውስጥ ያለው ግጭት ለመመልከት ነው የተሾሙት፡፡

ፌልትማን ከፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ሲወያዩ  በትግራይ ጉዳይ ስለ መወያየታቸው ምንም ዝርዝር መረጃ አላገኘንም፡፡

የኤርትራ መንግስት ከሰሙኑ ባወጣው መግለጫ  ምዕራባውያንና አሜሪካ የሚከተሉት ስትራቴጂ ምስራቅ አፍሪካን እየረበሸ ነው ማለቱን ይታወሳል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 29 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ