ደቡብ ኮርያ ለትግራይ 400 ሺህ ዶላር ድጋፍ ለዓለም ምግብ ፕሮግራም አደረገች

0
453

ከስድስት ወራት በላይ በቆየው የትግራይ ጦርነት ከ1.7 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል ይህም ተከትሎ ደቡብ ኮርያ በትግራይ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚሹ 400 ሺ ዶላር በዓለም ምግብ ፕሮግራም አደረገች፡፡

የተለገሰው ገንዘብ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በክልሉ አስቸኳይ ምግብ እና አልሚ ምግቦች ለሚያስፈልጋቸው ወደ 2.1 ሚሊዮን ሰዎችን ለመድረስ እያደረገ ያለውን ጥረት እንደሚያግዝ ተገልጿል።

የዓለም ምግብ ድርጅት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በትግራይ 91 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ፈላጊ ነው ሲል ማስታወቁ ሚዘነጋ ጉዳይ አይደለም፡፡

የሕፃናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ከቦታ ቦታ ቢለያይም ባለፉት ወራቶች አጣዳፊ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በትግራይ እየጨመረ መምጣቱን የድንበር የለሹ ሐኪሞች ድንገተኛ ቡድን አስተባባሪ ቶማሶ ሳንቶ ገልፆ ነበር።

ብዙ ቤተሰቦች የሚገኙበት የምግብ ጥራት እና ብዛት መቀነሱ ብዙዎች በቀን አንድ ጊዜ ብቻ መመገባቸውን በምክንያትነት አቅርበዋል፡፡

“በክልሉ የሰብአዊ ዕርዳታን ለማሳደግ እና ተደራሽነቱን ለማስፋፋት የሚጠይቅ አስቸኳይ ፍላጎት አለ” ብለዋል ሳንቶ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግስት ከአሁን በኋላ በትግራይ 92 ወረዳዎች ውስጥ ከሚደረጉ ሰብዓዊ ድጋፎች 14 በመቶውን ብቻ እንደሚሸፍን አስታወቀ፡፡

ቀሪው 86 በመቶው የዓለም ምግብ ፕሮግራምን ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ እርዳታ ሰጭ ተቋማት እንደሚሸፈን የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ገልጸዋል፡፡

በክልሉ በመደረግ ላይ ካለው ሰብዓዊ ድጋፍ 70 በመቶ ያሉ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው መባሉ የሚታወስ ነው፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 28 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ