አስመራና ካርቱም የሁለትየሽ ግንኝነት ለማጠናከር ተስማሙ

0
279

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ወደ ካርቱም ማቅናታቸውና ከሱዳን ባለስልጣናት ጋር መገናኘታቸው ይታወሳል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከሱዳን ባለስልጣናት ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሱዳን ትሪብዩን አስነብቧል።

በሱዳንም በኤርትራም በኩል ከወጡት መግለጫዎች ለመረዳት እንደተቻለው ከሆነ የሀገራቱ ወይይት እና ንግግር ትኩረት ያደረገው በሁለትዮሽ ግንኙነታቸው ላይ ነው።

በኤርትራ ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር በኩል በወጣው መግለጫ ሀገራቱ ፥ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚ፣ በደህንነት፣ በወታደራዊው ሴክተር የሚሰሩትን ስራ ለማጠናከር ስለመስማማታቸው ገልጿል፡፡ በሱዳን በኩል የወጣው መግለጫ ደግሞ ወይይቱ የሁለቱም ሃገራት ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው የሚል ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ከጀነራል አል ቡርሃን በተጨማሪ ከዶ/ር አብደላ ሀምዶክ ጋር በተናጠል የተወያዩ ሲሆን “የቀጠናው የኢኮኖሚ ውህደት የፖለቲካ ጉዳዮችን ለመፍታት የሚያስችል መንገድ ያመቻቻል” በሚል መስማማታቸውን ከሱዳን በኩል ተሰምቷል።

በኤርትራ ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር በኩል፥ “በቀጠናው ማዕቀፍ ውስጥ የኤርትራ እና የሱዳን የሁለትዮሽ ትስስር እንዲጠናከሩ በጥቂት ተጨባጭ፣ በፕሮጀክቶች ላይ ለማተኮር” መስማማታቸውን ይገልጻል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያሳ ወደካርቱም ከመሄዳቸው ቀድም ብሎ ከካርቱም በርካታ ሪፖርቶች በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ችግር ለመፍታት ያሸማግላሉ ሲባል የነበረ ቢሆንም እስካሁን በዚህ ጉዳይ ምንም የተባለ ነገር የለም።  

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 27 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ