“አሜሪካ የሱዳንን ሽግግር መንግስት ትደግፋለች”- ሴናተር ክሪስ ኩን

0
254

አሜሪካ የሱዳንን የሽግግር መንግስት እንደምትደግፍ የአሜሪካው ሰኔት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባል የሆኑት ሴናተር ክሪስ ኩን አረጋገጡ፡፡

የኮንግረስ ልዑክን በመምራት በካርቱም ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ሴናተሩ ጉብኝታቸው የአሜሪካ ሱዳን ወዳጅነት የሚያረጋግጥ እንደሆነም የሱዳን የዜና ወኪል ሱና ዘግቧል፡፡

ክሪስ ኩን ከሱዳን የፋይናንስና ምጣኔ ሀብት ሚኒስትር ጋር ከተወያዩ በኋላ ለመገናኛ ብዙሀን እንደገለጹት “አሜሪካ እሰካሁን 700 ሚልዮን ዶላር ለሱዳን  ድጋፍ አድርጋለች በቀጣይም የሱዳናውያንን ሁለንተናዊ መረጋጋት፣ደህንነት እና ሰላም የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ የምትቀጥል ይሆናል”ብለዋል፡፡

የልዑኩ ለሌላኛው ሴናተር ክሪስ ቫን ሆለን በሱዳን ያለውን የሽግግር በማድነቅ “ሱዳን ወደ ዴሞክራሲ፣ሰላም እና ፍትህ በምታደርገው ጉዞ አሜሪካ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ናት” ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 27 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ