በትግራይ ጉዳይ ጆ ባይደንና ልዑል አልጋ ወራሽ መሓመድ ቢን ዛያድ ተወያዩ

0
85

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ ልኡል አልጋ ወራሽ መሓመድ ቢን ዛያድ ጋር በስልክ በትግራይ ጉዳይ ላይ ተወያዩ፡፡

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከ ልዑል አልጋ ወራሽ ጋር የተወያዩት የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ 50ኛ ዓመት የነፃነት ቀን በማስመልከት ነው፡፡

የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ስለ ቀጠናውና ስለ አለማቀፍ ችግሮችን የተወያዩ ሲሆን የትግራይ ጦርነት በሚመለከትም ተወያይተዋል፡፡

በተለይም መሪዎቹ በትግራይ ክልል በጦርነት ምክንያት የተከሰተው የሰብአዊ እርዳታ ቀውስ ለመፍታትም አውርተዋል ነው የተባለው፡፡

ከወራት በፊት በተለያዩ ሀገራት ስለ ትግራይ ጦርነት አስመልክቶ የተደረገው ሰልፍ የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬትስ ከኤርትራ መንግስት እኩል ተወቃሽ እንደነበረች ሚዘነጋ ጉዳይ አይደለም፡፡

የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ በትግራይ ጦርነት ላይ ከኢትዮጰያና ኤርትራ መንግስት ጎን በመሰለፍ እንዲሁም ድሮን በመስጠት ድጋፍ አድርጋለች ተብላም ትታማለች፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 27 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ