ግብፅ ከፈረንሳይ 30 ዘመናዊ የጦር ጄቶችን ልትገዛ ነው

0
448

ፈረንሳይ በ4.5 ቢሊዮን ዶላር 30 የጦር ጄቶች ለግብፅ ለመሸጥ ተስማማች።

ግብፅ በ4.5 ቢልየን የአሜሪካ ዶላር 30 የራፋል የጦር ጄቶችን ከፈረንሳይ ልትገዛ ነው መሆኑን ሮይተርስ  በዘገባው አትቷል።

ፈረንሳይ የሚገኘው ዳሳውልት አቪዬሽን ለግብፅ 30 የራፋል የጦር ጀቶችን ሊሸጥ መስማማቱንና የጄቶቹ ጠቅላላ ዋጋ 4.5 ቢልየን ዶላር ነው ተብለዋል፡፡

የግብፅ የመከላከያ ሚኒስትር እንዳሉት ከሆነ ክፍያው ግብፅ በአስር አመት ለመክፈል መስማማቷ የገለፁ ሲሆን ስለ ስምምነቱ ግን ሰፋ ያለ ማብራርያ አልሰጡም ነው የተባው፡፡

ሚስጥራዊ ሰነዶችን በመጥቀስ ስምምነቱ  እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በፈረንጆቹ 2021 ሚያዝያ  መጨረሻ ላይ መደረጉን የተነገረ ሲሆን  የግብፅ ልዑካን ማክሰኞ ፓሪስ ሲደርሱ ሽያጩ በውልና ስምምነት ሊከናወን ይችላል ነው የተባለው።

ግብፅ የምትገዛው ይህ ጄት በሰአት 1,389 ኪ.ሜ ሲጓዝ ክብደቱ 9,979 ኪ.ግ  ሲሆን የክንፍ ስፋቱ ደግሞ 11 ሜትር ነው።

አንዳንድ የሰብአዊ መብት ተሟጓጋቾች አንደዚህ ያለ መሳሪያ ለግብፅ መሸጥ በሀገሪቱ ብዙ የሰብአዊ መብት ረገጣ እየፈፀመ ያለውን መንግስት ማበረታት ነው በማለት ፈረንሳይን ኮንነዋል።

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 26 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ