የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ውጤቱን ከምርጫ ቦርድ በፊት እኔ ይፋ ላድርግ ብሏል- ኢትዮጵያ

0
207

የአውሮፓ ህብረት ሀሳብ ኢትዮጵያ ከተቀበለችው ቅኝ ግዛት ነው ሲሉ ነው የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የተናገሩት።

የአውሮፓ ህብርት ምርጫውን አልታዘብም ያለው በራሱ ቅኝ ልግዛችሁና ላስተዳድራችሁ የሚል ሀሳብ እንጅ በኢትዮጵያ መንግስት ችግሮች አይደለም ያሉት አምባሳደሩ ህብረቱ በሁለት ነገሮች ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር መስማማት አልቻለም ብለዋል።

አንደኛው የአውሮፓ ህብረት የራሴን የቴሌኮም ሲስተም በማስገባት ምርጫውን መታዘብ እፈልጋለሁ ሲል ጠይቋል ነው የተባለው። ቃል አቀባዩ የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ የቴሌ ኮሙኒኬሽን ሲስተም የማያውቀው ሌላ የራሱን ሲስተም ዘርግቼ ምርጫው ልታዘብና ልከታተል ማለቱን ኢትዮጵያ አልተቀበለችውም ብለዋል።

ይህ ኢትዮጵያ ያላትን የቴሌኮም ሲስትተም ተጠቅሞ በራሷ ሀገር ምርጫየማድረግ መብቷን የሚጥስና የአውሮፓ ህብረት ፍላጎትን ለማስፈፀም ያለመ በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን አልቀበልም ብሏል ሲሉ ነው ቃል አቀባዩ የተናገሩት።

ሁለተኛው ከህብረቱ ጋር ኢትዮጵያን ያላስማማት ጉዳይ የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ የምታደርገው 6ተኛ ሀገራዊ ምርጫ ውጤት ከምርጫ ቦርድ በፊት ውጤቱን ቀድሜ የመግለፅ እድል ይሰጠኝ በማለቱ ነው።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንደተናገሩት ህብረቱ የምርጫውን ውጤት ቀድሜ እንደገልፅ ከኢትዮጵያ ተቋሞችና ከምርጫ ቦርድ በፊት እድልና መብት ይሰጠኝ ማለቱ ላስተዳድራችሁ ወይም ቅኝ ግዛት ልግዛችሁ ከማለት እኩል ነው ብለዋል።

ይህንን ሀሳብ ለመቀበል ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ለመገዛት ማመን አለባት ወይም ደግሞ ባለፉት ጊዚያት ያልተደረገውን ለማድረግ መወሰን አለባት ማለት ነው፤ ይህ ደግሞ ፈፅሞ አይሆንም ሲሉ ነው የተናገሩት።

ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት አመታት ምርጫ ስታደርግ ይህንን አልፈቀደችም ስለሆነም በራሳችን የቴሌኮም ሲስተም ተጠቅመው መታዘብ ይኖርባቸዋል ፤ እንዲሁም የምርጫ ውጤት የሚገለፀው በራሳችንና በሚመለከተው ተቋም ነው በሚል መንግስት አቋም በመያዙ ህብረቱ አልታዘብም ብሏል ነው የተባለው።

አምባሳደር ዲና የህብረቱ ፍላጎት ቤትህ ውስጥ ገብቶ አንተ መደብ ተኛ እኔ አልጋው ላይ የሚል የቅኝ ገዥ ፍላጎት ነው ብለዋል።

ዘጋቢ- በቃሉ አላምረው

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 26 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ