የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ ለምታደርገው ምርጫ ታዛቢዎች አልክም አለ

0
261

የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ ግንቦት መጨረሻ ላይ ለምታርገው ምርጫ 14 የህብረቱ ታዛቢዎች ለመላክ የነበረው እቅድ ሰርዣሎ ብለዋል፡፡

የአውሮፓ ሕብረት የውጪ ጉዳዮች እና የደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ የሆኑት ጆሴፍ ቦሬል እንዳስታወቁት ከሆነ ህብረቱ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ቁልፍ በሆኑት የምርጫ መስፈርቶች ላይ ስምምነት አለመደረሱ ነው የገለፁት፡፡

ኢትዮጵያ በቀጣይ ወር የምታደርገውን የፓርላማ አባላት ምርጫ ለመታዘብ ህብረቱ ሁኔታዎች ስላልተሟሉ በቦታው ተግኝቶ ለመታዘብ ማሰቡን ሰርዝዋ ብለዋል፡፡

ምርጫ መደገፍ ዴሞክራሲ መደገፍ መሆኑን ህብረቱ ያምናል ያለው መግለጫው ዝቅተኛ የሆኑ መስፈርቶችንና የምርጫ ሂደቶች ያልተሟሉበት ከመሆንም በላይ ለህብረቱ ታዛቢዎች  አሁን ያለው የፀጥታ ሁኔታ  አስጊ ነው ልለዋል፡፡

ይህ የኢትዮጵያ የፀጥታ ችግር በምርጫው ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አሳድርዋል ያለው ህብረቱ በተለይም መራጮች እንዳይ መዘገቡ እድርግዋል ነው ያለው፡፡

ህብረቱ እንዳለው ከሆነ ኢትዮጵያውያን ለዲሞክራሲ ሲሉ ለሚያደርጉት ምርጫ  ለመደገፍ የሚያስችል አስተማማኝ የሆነ ዋስትና በሂደቱም ሆነ በምርጫው ተአማኒነት አላገኘሁም ብለዋል፡

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት፤ ዜጎችና ፖለቲከኞች መብታቸው የሚያረጋግጡበት ምርጫ እንዲኖር እደግፋለሁኝ ያለው ህብረቱ ተአማኒነት ያለው አሳታፊና እዉነተኛ የሆነ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ ያቀረበው ሲሆን ይህንንም ለማገዝ ገና ከጅምሩ 20 ሚሊዮን ይሮ መስጠቱ አስታውስዋል፡፡

የሕብረቱን መግለጫ ተከትሎ በኢትዮጵያ በኩል የተባለ ነገር የለም።

ይህ እንዲህ እንዳለ አምስት የአሜሪካ ሴናተሮች ኢትዮጵያ የምታካሂደው ምርጫ አሁን ባለበት ሁኔታ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን አያሟላም ማለታቸውም ይታወሳል።

ሴናተሮቹ ይህን ያሉት በቅርቡ የፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ለተሾሙት አምባሳደር ጆፍሪ ፌልትማን በጻፉት ደብዳቤ ነው።

ኢትዮጵያ ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 2013 ዓ.ም. ለማካሄድ ላቀደችው ስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎችን ያስመዘገቡ ሲሆን መራጮችም እየተመዘገቡ ይገኛሉ።

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 26 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ