ቢል ጌትስ እና ባለቤቱ ሚሊንዳ ጌትስ ከ 27 ዓመታት የትዳር ሕይወት ብኋላ ተለያዩ

0
183

ቢልየነሮቹ ቢል ጌትስ እና ባለቤቱ ሚሊንዳ ጌትስ ከ27 ዓመታት በፊት የመሰረቱትን ትዳር ማፍረሳቸውን ይፋ አደረጉ።

ቢል ጌትስ እና ባለቤቱ፤ ”ከዚህ በኋላ እንደ ጥንዶች ሆነን መቀጠል አንችልም” ብለዋል።

”ከብዙ ማሰብና ግንኙነታችንን ለማሻሻል ከሰራን በኋላ ትዳራችንን ማፍረሱ የተሻለ አማራጭ አድርገን ወስደናል” ብለዋል በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስቀመጡት መልዕክት።

ሁለቱ ጥንዶች የተገናኙት በአውሮፓውያኑ 1980ዎቹ ውስጥ ሚሊንዳ የቢል ጌትስን ማይክሮሶፍት ተቋም በተቀላቀለችበት ወቅት ነበር።

ቢሊየነሮቹ ጥንዶች በ27 ዓመታት የትዳር ዘመናቸው ሦስት ልጆችን ያፈሩ ሲሆን፤ በተለያዩ ዘርፎች ድጋፍ የሚያደርገውን ‘ቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን’ አቋቁመዋል።

ድርጅታቸውም የተለያዩ አይነት ተላላፊ በሽታዎችን ለመዋጋትና ለህጻናት ክትባቶችን ለማድረስ በቢሊየኖች የሚቆጠር ዶላር ፈሰስ አድርጓል።

ቢል ጌትስ በፎርብስ መጽሄት መረጃ መሠረት የዓለማችን አራተኛው ቢሊየነር ሲሆን የተጣራ ሀብቱም 124 ቢሊየን እንደሆነ ተነግሯል።

ቢል ጌትስ በአውሮፓውያኑ 1970ዎቹ ውስጥ ከባልደረባው ጋር በመሆን በዓለማችን ትልቁ የሶፍትዌር ድርጅት የሆነውን ማይክሮሶፍትን በመክፈት ነበር የጀመረው።

ጥንዶቹ በትዊተር ገጻቸው ላይ ለተከታዮቻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ “ባለፉት 27 ዓመታት አስገራሚ የሆኑ ሦስት ልጆችን አሳድገናል፤ በመላው ዓለም የሰዎችን ችግር ለመፍታት የሚሰራ ድርጅት አንድ ላይ መስርተናል” ብለዋል።

”አሁንም ቢሆን በዚህ ዓላማ ማመናችንን አናቆምም፤ በፋውንዴሽኑ ዙሪያ አንድ ላይ መስራታችንን እንቀጥላለን። ነገር ግን ከዚህ በኋላ በሚኖረን ቀሪው የሕይወታችን ዘመን እንደ ጥንዶች ሆነን መቀጠል እንደማንችል ተስማምተናል” ብለዋል።

አክለውም ” ቤተሰባችን ይህንን አዲስ የሕይወት ምዕራፍ በሚጀምርበት ወቅት የግል ህይወታችን ላይ ጣልቃ እንዳትገቡ እንጠይቃለን” ብልዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧታል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 26 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ