በትግራዩ ግጭት 5ሺህ ሕጻናት ከወላጆቻቸው ተለይተዋል – የህፃናት አድን ድርጅት

0
153

የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት አድን ድርጅት በትግራዩ ግጭት ምክንያት ወደ 5ሺህ የሚጠጉ ሕጻናት ከወላጆቻቸው ጋር ተለያይተዋል አለ።

ሕጻናት አድን ድርጅቱ እንዳለው ከወላጆቻቸው የተለዩ ሕጻናት በስደተኛ እና ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ።

ሴቭ ዘ ቺልድረን እንደሚለው ከወላጆቻቸው የተለዩት ሕጻናት ለረሃብ፣ ለአካላዊ እና ጾታዊ ጥቃቶች ተጋላጭ ናቸው።

ድርጅቱ የሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ለበርካታ የክልሉ ስፍራዎች እርዳታ ማቅረብ ባለመቻላቸው፤ ሕጻናቱ ያለማንም ድጋፍ እራሳቸውን ለመርዳት ጥረት ያደርጋሉ ብሏል።

ከስድስት ወራት በላይ በቆየው የትግራይ ጦርነት ከ1.7 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግጭቱ በክልሉ የከፋ የሰብዓዊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል ሲል ያስጠነቅቃል።

ተመድ ሕጻናት፣ የሚያጠቡ እና ነብሰ ጡር እናቶች ከፍተኛ የሆነ የምግብ እጥረት እያጋጠማቸው ስለመሆኑ የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ ይላል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ የአፍሪካና የተቀረው ዓለም መሪዎች በትግራይ ስላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድምፃቸውን የበለጠ እንዲያሰሙ ጥሪ አቅርቧል።

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ለስድስት ወራት በዘለቀው የትግራይ ጦርነት በርካታ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተፈጽመዋል ብሏል።

አምነስቲ፤ ‘ኦፕን ሶርስ’ የተሰኘ የምርመራ መንገድ እንዲሁም የሳተላይት ምስሎች ትንተና እና የቪድዮ ምስሎች ማስረጃዎችን በመጠቀም የተለያዩ ጥሰቶችን እንደ መዘገበ በመግለጫው አሳውቋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧታል።

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 26 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ