ምዝገባ ባልተጀመረባቸው የምርጫ ክልሎች ምዝገባ እንዲጀመር ተወሰነ

0
177

የመራጮች ምዝገባ ሒደት ባልተጀመረባቸው የምርጫ ክልሎች ምዝገባው በልዩ ሁኔታ እንዲከናወን መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ቦርዱ በምዝገባ ሂደቱ የሚያጋጥሙ የተለያዩ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እያካሄደ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

የምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተው የመራጮች ምዝገባ ባልተጀመረባቸው ቦታዎች ምዝገባውን ለማስጀመር ከክልል መስተዳድር አካላት ጋር በመተባበር ጥረት ሲያደርግ እንደነበር ያስታወሰም ሲሆን ምዝገባው ከሚያዝያ 29 – ግንቦት 13 ቀን 2013 ድረስ በልዩ ሁኔታ እንዲከናወን ስለመወሰኑ ገልጿል።

በውሳኔውም መሰረት በምእራብ ወለጋ (ከቤጊ እና ሰኞ ገበያ ምርጫ ክልል ውጭ)፣ በምስራቅ ወለጋ ዞን (ከአያና እና ገሊላ ምርጫ ክልል ውጪ)፣ በቄለም ወለጋ እና በሆሮ ጉድሩ ዞን (ከአሊቦ፣ ጊዳም እና ኮምቦልቻ ምርጫ ክልል ውጪ) ከሚገኙት 31 ምርጫ ክልሎች መካከል በ24ቱ ምዝገባው የሚከናወን ይሆናል፡፡

ምዝገባው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማሽ ዞን ከሚገኙ አምስት የምርጫ ክልሎች ከሴዳል ምርጫ ክልል ውጪ በአራቱ እንዲካሄድም ተወስኗል፡፡

ሴዳል ወረዳ ሙሉ በሙሉ በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር እንደዋለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡

ዳዋ ጨፋ፣ ጨፋ ሮቢት እና ባቲን በመሳሰሉ የአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አካባቢዎች የሚገኙ መራጮችም በእነዚሁ ቀደም ሲል በተጠቀሱት ቀናት በልዩ ሁኔታ ይመዘገባሉ ተብሏል፡፡

ቦርዱ ፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ሚዲያ እና ሲቪል ማህበራት ለምዝገባው ስኬት መረጃን በመስጠት እንዲተባበሩ ጠይቋል፡፡

አጣዬን መሰል ከተሞች በወደሙበት በሰሞነኛው የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን እና የሰሜን ሸዋ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች ጥቃት በርካቶች መሞታቸው እና መፈናቀላቸው አይዘነጋም፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 26 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ