የኤርትራ ወታደሮች ወደ ትግራይ የሚሂድ እርዳታ እየዘረፉና መንገድ እየዘጉ ነው ተባለ

0
440

በትግራይ ክልል የኤርትራ ወታደሮች ወደ ዓዲጋራትና አክሱም የሚወስድ መንገድ በመዝጋት የእርዳታ ምግብ እየዘረፉ ነው ሲል ኤ ኤፍ ፒ ዘግቧል፡፡

በትግራይ ክልል የኮማንድ ፖስት ኃላፊ ጄነራል ዮውሃንስ ገ/መስቀል ላለፉት ሁለት ሳምንታት እርዳታውን ለማዳረስ ችግር ገጥሞን ነበር ፤ በተለይም በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ላይ ያሉት ቦታዎች አስቸጋሪ ሁነዋል ብለዋል፡፡

ከሁለት ሳምንታት ጀምሮ ወደ አኩስምና ዓዲግራት የሚወስደው መንገድ በኤርትራ ወታደሮች መዘጋቱ ጀነራሉ ገልፀዋል ሲል ነው ኤ ኤፍፒ የዘገበው፡፡

ይህ በመሆኑም አሁንም ቢሆን የትግራይ ህዝብ በርሃብ እየተጎዳ መሆኑን የተለያዩ የአለማቀፍ የሰብአዊ ድርጅት ተቋማት አየገለፁ ይገኛሉ፡፡

ሚያዝያ 15 በደቡባዊ ምብራቅ ትግራይ ግጀትና ሳምረ የእርዳታ ሰራተኞች በማባረር እርዳታ ለመቀበል የመጡ ሰዎች በመበተን የእርዳታ እህሉ በኤርትራ ወታደሮች እንደተወሰደ ነው የተገለፀው፡፡

አንድ ስሙን መናገር ያለፍለገ ሰው ለኤ ኤፍ ፒ እንደተናገረው ከሆነ የሰብሰዊ እርዳታ ሰራተኞች የትግራይ ህዝብ እንዲራብና እንዲጠማ እየተደረገው ያለው ጥረት ሰራተኞቹ እንዲያለቅሱና እንዲያዝኑ አድርጋችዋል ሲል ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ሙሉ ነጋ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ስለ ጉዳዩ ሲጠየቁ ህዝቡ ስለ መንገድና ስለ እርዳታ ክፍፍሉ እያማረረ ነው ፤ ለዚህም ከፍተኛ ባስልጣናት ጉዳዩን እየተመለከቱት ነው የሚል ምላሽ ነው የሰጡት፡፡

ከስድስት ወራት በፊት በትግራይ ክልል የተጀመረው ጦርነት መንግስት የኤርትራ ወታደሮች በጦርነቱ መሳተፋቸው ክዶ ቢቆይም ባሳለፍነው ወር ግን ሙሉ ለሙሉ የኤርት ወታደሮች በትግራይ መሬት መኖሯቸው አምንዋል፡፡

የኤርትራ መንግስት በወገኑ ልክ እንደ ኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ ወታደሮች በተመለከተ ክዶ ቢቆይም ባሳለፍነው ሳምንት ግን የኤርትራ አምባሳደር ለፀጥታው ምክርቤት በፃፉት ደብዳቤ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ላይ መኖራቸው ለመጀመርያ ጊዜ አምኖ እንደሚያሰወጣ ቢገለፁም እሁንም በህዝብ ላይ የተለያዩ በደሎች እያደረሱ እንዳሉ ተገልፀዋል፡፡

አምንስቲ ኢንተርናሽናልና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሙሽን በትግራ ክልል አክሱም ከተማ የኤርትራ ወታደሮች ጭፍጨፋ መፈፀማቸው ቢገልፀም የኤርትራ መንግስት ግን ሙሉ ለሙሉ ድርጊቱ ወታደረቹ እንዳልፈፀሙት ነው የገለጸው፡፡

የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ማርክ ሎኮክ ለፀጥታው ምክር ቤት በትግራይ ክልል ኦፍላ ወረዳ 150 ሰዎችበረኃብ መሞታቸው ገልፆ ነበር ሁኖም የኢትዮጵያ መንግስት ይህ ከእውነት የራቀ ነው ሲል አጣጥሎታል፡፡

በተጨማሪም ዘ ኢኮኖሚስት የአለም የሰላም ፋውዴሽንን መረጃ በመጥቀስ ባወጣው መረጃ መሰርት በትግራይ ክልል ወታደሮች ወደ ህዝብ እርዳታ እንዳይ ደርስ እያረጉ መሆናቸው ገልፆ ቢያንስ በቀን ከ50 እስከ 100 ሰዎች እንደሚሞቱ በድረገፁ አስነብቦ ነበር፡፡

የኤርትራ ማስታወቅያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገ/መስቀል የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ለእርዳታ የተባለው ምግብ በመዝረፍ ሰዎች በርሃብ እንዲጎዱ እየተደረገ ነው ተብሎ የተጠየቁት ጥያቄ የኤርትራ ወታደሮች ይህንን ድርጊት አልፈፀሙም ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ ወታደሮች አስወጣሎ ከማለት ውጪ ምነም መሬት ላይ ጠብ ያለ ነገር የለም እንዲሁም ከሰሞኑ አንቶንዮ ብሊንከን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ጋር በመደወል የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ህዝብ ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየፈፀሙ ስለሆነ ተሎ መውጣት እንዳለባቸው ጭምር እሳሰቦ ነበር። ሁኖም ጠቅላይ ሚኒስተሩ ይህንን በተመለከተ እስካሁን ያሉት ነገር የለም።

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 21 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ