አሜሪካ በዚህ ሳምንት በ4 የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ጉብኝት የሚያደርግ ልዑክ ልትልክ ነው

0
66

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት የሚያደርግ ከፍተኛ ልዑክን በዚህ ሳምንት ወደ አራት የቀጣናው ሃገራት ይልካሉ ተባለ፡፡

ልዑኩ በሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (ዩኤኢ)፣ ግብጽ እና ዮርዳኖስ ጉብኝት እንደሚያደርግም አሽራቅ አል አውሳት የኋይት ሃውስ የመረጃ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

አሽራቅ አል አውሳት በጉብኝቱ ልዑኩ በወቅታዊ ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ያደርጋልም ነው ያለው፡፡

ምክክሩ የኢራንን የኒውክሌር መርሐ ግብር፣ የዩኤኢን የቀጣዩን ትውልድ የኤፍ-35 የጦር ጄቶች ግዢ ጉዳይ እንዲሁም ሌሎችንም የቀጣናውን አንገብጋቢ ጉዳዮች ሊያካትት እንደሚችልም ተነግሯል፡፡

ፕሬዝዳንት ባይደን አንድ መቶ የስልጣን ቀናትን ነገ ያስቆጥራሉ፡፡

ይህን ተከትሎ ዛሬ በጋራ ለተሰበሰበው የሃገሪቱ ምክር ቤት (ሴኔት እናኮንግረስ) የመጀመሪያ ማብራሪያቸውን ሰጥተዋል፡፡

በማብራሪያቸው ሃገራቸው የኮሮና ወረርሽኝን ጨምሮ የገጠመማትን መጥፎ አጋጣሚዎች ወደ መልካም ዕድል መቀየር ስለሚቻልበት ሁኔታ አንስተዋል፡፡

ባይደን ከቻይና እና ሩሲያ ጋር ግጭት ውስጥ መግባት እንደማይፈልጉ ቢገልጹም ጠንከር ያለ አቋም እንደሚኖራቸውና ጠንከር ያሉ እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ግን አልሸሸጉም፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 21 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ