አቶ ተኮላ አይፎክሩ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ተሸሙ

0
214

በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ተኮላ አይፎክሩ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንን እንዲመሩ መሾማቸው ታወቀ።

አቶ ተኮላ ከትናንት ሚያዚያ 19/2013 ዓ.ም ጀምሮ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው መመደባቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል ።

የቀድሞው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ከሁለት ዓመታት በላይ በኃላፊነቱ ሲሰሩ ቆይተዋል።

አዲሱ ኮሚሽነር አቶ ተኮላ ከሦስት ዓመት በፊት በፌደራል ፖሊስ ውስጥ በኃላፊነት ከመመደባቸው አስቀድሞ በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በተለያዩ ቦታዎች አገልግለዋል።

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶችና በተፈፀሙ ጥቃቶች የበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ ነው አቶ ተኮላ ወደ ኃላፊነት የመጡት።

በተለይ በሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች በታጣቂዎች ተፈፀመ በተባለው ጥቃት ቁጥሩ በውል የማይታወቅ የሰው ሕይወት አልፏል፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩም ከቀያቸው መፈናቀላቸው ተገልጿል።

ሮይተርስ አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣንን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ‘በግጭቱ’ 200 ያህል ሰዎች መገደላቸውን ዘግቧል።

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች በክልሉም ሆነ ከክልሉ ውጪ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን ግድያና መፈናቀል የሚያወግዙና እንዲቆም የሚጠይቁ የተቃውሞ ሰልፎች ባለፈው ሳምንት ለተከታታይ ቀናት ተካሂደዋል።

አቶ ተኮላን ወደ ክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አመራርነት ያመጣቸው በጸጥታው መዋቅር ላይ የተደረገ ግምገማን ተከትሎ ሊሆን ይችላልም ተብለዋል።

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 20 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ