ጅማ ዞን ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ ’20 ሰዎች መገደላቸው’ ተነገረ

0
303

ጥቃቱ አርብ ሚያዝያ 15/2013 ዓ.ም ሊሙ ኮሳ ወረዳ፣ ቀጮ ክርክራ እና ጋሌ በተባሉ ቀበሌዎች ውስጥ የተፈጸመ ሲሆን ቢያንስ 20 ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን ኢሰመኮ መግለፁን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ውስጥ በሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች  በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ሰዎችን መግደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገልጿል።

ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ውስጥ በሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች  በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ሰዎችን መግደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገልጿል።

“…የፀጥታ ኃይሎች የደረሱት ታጣቂዎቹ ጥቃት ፈጽመው በስፍራው በርካታ ንፁሃን ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ነው” አቶ ኢማድ ቱኔ (የኢሰመኮ ከፍተኛ አማካሪ )

የኮሚሽኑ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት አቶ ኢማድ ቱኔብ እንደተናገሩት ፤ ከዚያ ክስተት በኋላ በነዋሪዎች ላይ ተጨማሪ ጥቃት እንዳይደርስ ለመከላከል መቻሉን ጠቅሰው ባለፉት ቀናት የፀጥታ ኃይሎች በተለይ በጅማ ዞን ተሰማርተው ጥቃቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን አመልክተዋል።

ኮሚሽኑ ጥቃቶቹን ተከትሎ ወደ አካባቢዎቹ ባለሞያዎችን ለማሰማራትና የደረሰውን ጉዳት በትክክል ማጣራት አለመቻሉን ተናግረዋል።

ከአካባቢው ባሰባሰበው መረጃ በጅማ ዞን የተፈጸመው ጥቃት የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን የሚያመለክት መረጃ እንዳገኘ አቶ ኢማድ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ኢሰመኮ ጥቃት እንደተፈጸመበት የገለጸው የአማሮ ልዩ ወረዳ የሰላም እና ደኅንነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ኤሊያስ ይልማ ጉዳትና ዝርፊያ መፈጸሙን አረጋግጫሎ ብለዋል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 19 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ