የትግራይ ህዝብ ተወሯል – ሳልሳይ ወያነ ትግራይ

0
859

“የትግራይ ህዝብ ተወሯል”  እኛም በአዲሱ የትግል ምእራፍ ላይ እንገኛለን ሲሉ የሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) ምክትል ሊቀመንበር አቶ አሉላ ሀይሉ ተናግረዋል፡፡

ምክትል ሊቀመንበሩ አከሎም እንደ ትግል ቆጥረን አዲስ የዲፕሎማሲ ስራዎች እየሰራን ነውም ብለዋል፡፡

እንደ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በመሆን  ህዝቡ እያጋጣመዉ ካለዉ  ችግር እንዲወጣ ሰላማዊ ትግል እያደረግን ነዉም ብለዋል ምክትል ሊቀ መንበሩ፡፡

በትግራይ ክልል ያለዉ ጦርነት ሕዝባዊ ትግል ሆነዋል ያሉት አቶ አሉላ የትግራይ ህዝብ እየደረሰበት ያለዉ ግፍ የአለም ማህበረሰብ እንዲያቀዉና የሰብአዊ እርዳታ እንዲያገኝ እንዲሁም ሚድያዎች በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለዉን ግፍ  እንዲዘግቡ የማስተባበር ስራ እየሰሩ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ትግራይ ከወራሪ ሀይሎች ነጻ እስክተወጣ እና የትግራይ ህዝብ የመረጠዉ መንግስት እስኪ መራው  እንደ ፓርቲ ሆነ እንደ ግለሰብም እየሰራን ነዉ ብለዋል፡፡

ከአምስት ቀናት በፊት የሳወት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አሉላ ሀይሉና የፓርቲዉ የፋይናንስ ክፍል አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ካሕሳይ ሀይሉ  በሰሜን እዝ ወታደሮች መወሰዳቸዉ መዘገባችን ይታወሳል ፡፡

ሁለቱም የፓርቲዉ አባላት ሰሜን እዝ አካባቢ የሚገኘዉ ህብር ኮሌጅ በሚባለዉ ቦታ ለአንድ ቀን እንዲያድሩ ከተደረገ በኋላ በሚወቀጥለዉ ቀን አርብ መፈታታቸዉ አቶ አሉላ ለአዉሎ ሚድያችን ነግረዉናል፡፡

አቶ አሉላና አቶ ካሕሳይ  በወታደሮቹ ከተወሰዱ በኋላ ስልካቸዉ እንደ ተወሰዱባቸዉ የነገሩን ሲሆን ለምን እንደታሰሩ ቢጠይቁም መልስ ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱም የፓርቲዉ አባላት ያለ ምንም ምክንያት ታስረዉ ያለ ምንም ምክንያት እንደተፈቱ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 19 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ