ለፉከራ ምላሽ መስጠት ጥሩ አይደለም – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

0
239

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሱዳን ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የህዳሴ ግድብ ከሞላች ወደ ክስ እሔዳለሁ ብላለች ፤ ኢትዮጵያ ግን ለዚህ ፉከራ ምላሽ አትሰጥም ሲሉ ዛሬ ተናግረዋል።

ለፍከራ ምላሽ መስጠት ጥሩ አይደለም ፤ ለፉከራ ምላሽ ከሰጠን ነገሩን ማበላሸት ነው ያሉት ቃል አቀባዩ ግድቡ ገና ሲጀመር የተጀመሩ ፉከራዎችን መልስ አንሰጥም በሂደት ውጤቱን ማየት ተመራጭ ነው ብለዋል።

ግድቡን ከጅመሩ ጀምሮ እንመታዋለን እናፈርሰዋለን የሚሉት አሁንም የቀጠሉት ወደ ፍርድ ቤት ሲሄዱ ያኔ በፍርድቤቱ ኢትዮጵያ መልስ ትሰጣለች ብለዋል አምሳደር ዲና ሙፍቲ።

ኢትዮጵያ የሶስትዮሽ ድርድሩ እንዲቀጥል ከፍተኛ ፍላጎት ስላላት ለዚህም እየሰራች ነው ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የተጀመረው የሶስትዮሽ ድርድር በቅርቡ እንዲቀጥል ፍላጎት አለን ብለዋል ።

ቃል አቀባዩ አምሳደር ዲና ዛሬ ሳምንታዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን የሶስትዮሽ ድርድሩ በቅርቡ እንዲቀጥል ኢትዮጵያ ፅኑ ፍላጎት አላት ብለዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ድርድሩን እየመራች ያለችውና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሆነችው ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ድርድሩ ድጋሜ እንዲጀመርና እንዲቀጥል ትሰራለች የሚል እምነት አላት ብለዋል።

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 19 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ