ግብፅና አረብ ኤምሬቶች በህዳሴ ግድቡ ላይ የጋራ አቋም ለመያዝ ተስማምተዋል

0
294

ግብፅና አረብ ኤምሬቶች በህዳሴ ግድቡ ላይ የጋራ አቋም ለመያዝ ተስማምተዋል ሲል ኢጅብት ቱደይ  ዘግቧታል፡፡

የአቡዳቢው ልኡል አልጋ ወራሽ ሼክ መሐመድ ቢን ዛያድ ወደ ግብፅ ካይሮ በመሔድ ከአብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር በመነጋገር ሚስጥራዊ ስምምንተ አደርገዋል

የግብጹ ፕሬዝደንት አብደል ፈታህ አልሲሲ የተባበሩት የአረብ ኤምሬቶች አልጋ ወራሽ ሼክ መሀመድ ቢን ዛያድን አግኝተዉ ስለ የህዳሴ ግድቡ ግንባታን በተመለከተ ወደ ጽህፈት ቤታቸዉ ጠርተዉ እንዳወሩና እንደተስማሙ ነው የተነገረው።

የፕሬዝደንት ሲሲ ቃል አቀባይ የሆኑት ባሳም ራዲ ሼክ መሀመድ ቢን ዛያድን ካይሮ በሚገኘዉ አለም አቀፉ የአዉሮፕላን ማረፍያችን በክብር ተቀብለናል ሲሉ ተናግረዋል።

የአቡዳቢ መሪ ግብጽን የሚያስጨንቃት የአባይን ጉዳይ ችግርሽ ችግሬ ነዉ ብለዉ ለመመከር አባሎቶቻቸዉን በማስከተል ካይሮ ገብተው ከግብፅ መሪዎች ጋር ስምምነት ፈፅመዋል ነው የተባለው።

ኢጅብት ቱ ደይ የተሰኘው የዜና አውታር እንዳሰራጨው መረጃ ከሆነ የሲሲ ቃል አቀባይ ራምዲ እንደሚሉት ፕሬዝደንቱ ግድቡን በተመለከተ ሁለቱም ግብጽና ሱዳን በማይጎዱበት ሁኔታ ለመፍታት አልጋ ወራሹ ይፈልጋሉ ለዚህም ያግዛሉ ብለዋል።

በተጨማሪም ሁለቱም መሪዎች በጎረቤት ሀገራት እየተፈጠሩ ያሉትን ግጭቶች ለመፍታት እንዴት እጃቸዉን አስገብተዉ መፍታት ይችላሉ በማለት ፖለቲካዊ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

የተባበሩት የአረብ ኤምሬቶች ባለፈዉ ወር በሶስቱ ሀገራት ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ ያለዉ አለመግባባት ለመፍታት ሸምጋይ እንሁን ብለዉ ነበር፡፡ ትኩረት ያደረጉበት ደግሞ ሱዳንና ግብጽ ሳይጉዱ የዉሀ ሙሊት የሚከናወንበትና ግንባታዉ የሚቀጥልበትን መፍትሄ ላበጅ ብትልም ኢትዮጵያ አሻፈረኝ ማለቷ ይታወሳል፡፡ ከአፍሪካ ህብረት ዉጪ ምንንም አሸማጋይ አልፈልግም በማለት ኢትዮጵያ የአረብ ኤምሬቶች አስታራቂነት ተቋዉማለች፡፡

የመጀመሪያዉ 4.9 ቢሊዮን ኪውቢክ ሜትር የዉሀ ሙሌት ያከናወነችዉ ኢትዮጵያ አሁንም ሁለቱም ሀገራት ይስማሙ አይስማሙ ሁለተኛዉ የዉሀ ሙሌት ለማድረግ ዝግጅቴን ጨርሻለሁ የምትለዉ ኢትዮጵያ፣ ከግብጽና ሱዳን ሀይለኛ ተቋሞ ከመምጣቱ በላይ ሱዳን እከስሻለሁ ግብጽ እዘምታለሁ የሚል ዛቻ በሚድያዎቻቸዉ አስተላልፈዋል፡፡

ታድያ የአረብ ኤምሬቶች ሶስትንም ሀገራት በማይጎዳ መንገድ ችግሩን እንፍታና እንዴት እናግዝ በማለት ነዉ ወደ ግብጽ ያመሩት፡፡

ሁለቱም መሪዎች በተገናኙበት ባለፈዉ ቅዳሜም የግብጽና የተባበሩት ኤምሬስ የአረብ ብሄራዊ ደህንነትና ለኡላዊ ሀገራቱ የዉጭ ጣልቃ ገብነት ለመከላከል የአብረን እንስራ ስምምነት ላይ ድርሷል፡፡

የሁለቱም ስምምነት ግድቡን በተመለከተ ምን ድረስ ላይ ጣልቃ ለመግባት እንደተስማሙ በሁለቱም ወገኖች የተባለ ነገር የለም፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 18 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ