“በጥቃቱ የመንግሥት መዋቅር ጭምር ተሳትፏል” – አቶ አገኘሁ ተሻገር

0
405

በአማራ ክልል በተፈጸሙ ጥቃቶች አመራሩ የነበረው ሚና እያተጣራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ገለጹ

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር ትላንት ማምሻውን ለሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ ፣ በጥፋቱ አመራሮችም መሳተፋቸውን የተመለከተ ጥቆማ በመኖሩ የማጣራት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ማንነትን መሰረት በማድረግ የተፈጸሙትን ጥቃቶች አስቀድሞ መከላከ ያልተቻለበት ምክንያትም እየተጣራ እንደሚገኝ ርእሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

በጥቃቱ የመንግሥት መዋቅር ጭምር ተሳትፏል ብለዋል። “እኛም መዋቅራችንን እየፈተሽን ነው፣ ይህ ሁሉ ውድመት ሲከሰት የጸጥታ ኀይላችን የት ነበር፣ የመረጃ እና የደኀንነት መዋቅራችን የት ነበር የሚለውን እያጣራን ነው” ብለዋል በሰጡት መግለጫ።

በጥቃቶቹ የደረሰው የጉዳት መጠንም በቀጣይ ተጣርቶ እንደሚገለጽ ጠቁመዋል፡፡

ጥቃቱን ተከትሎ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች የተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች በአብዛኛው ሰላማዊ እንደነበሩ የተናገሩት አቶ አገኘሁ ፣ በባህርዳር ግን የዝርፊያ እና የንግድ ተቋማትን የመዝጋት ሙከራዎች እንደነበሩ አንስተዋል።

ይሁንና አሁን ላይ የከተማዋ እንቅስቃሴ ወደነበረበት እንደተመለሰ ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለጹት፡፡

“ሕብረተሰቡም ይህን ለመቃወም ሞት በቃ ለማለት ሳር አንኳን ሳይረግጥ በሰላም ሀሳቡን መግለጹ ተቀባይነት ያለው ነው” ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የሰለፉን ዓላማ አንዳንድ ኀይሎች ለመጥለፍ ሙከራ አድርገው ነበር ብለዋል።

በዚህም ሕዝብን ለማለያየት የወጣው መልእክት የአማራን ሕዝብ እና የሰልፉን ዓላማ እንደማይወክል ተናግረዋል።

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 15 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ