ቀይ መስቀል በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ የደረሰው “አስደንጋጭ” ፆታዊ ጥቃቶች አወገዘ

0
635

መቀመጫው ጀኔቫ ያደረገው የአለማቀፍ የቀይ መስቀል ማህበር በትግራይ ክልል ውስጥ የሴቶች ጥቃት አየተስፋፋ በመምጣቱ እጅግ እንዳሳሰበው ገልፆ እንዲሁም ድርጊቱን አውግዝዋል፡፡

ጦርነቱ አሁንም በትግራይ ክልል በመቀጠሉ አስገድዶ መደፈር እንደ ጦር መሳርያ ሊያገለግል ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው የአለማቀፍ ቀይ መስቀል ማህበር ዋና ዳይሬክተር ሮቦርት ማርዲኒ ተናግረዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ እንዳሉት ከሆነ በክልል የሚገኙት ሆስፒታሎችና ጤና ጣብያዎች ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች በየ ቀኑ ሪፖርት አያደረጉ ነው ብለዋል፡፡

እስካሁን ሪፖርት የተደረጉ ፆታዊ ጥቃቶች እጅግ በጣም አስደንጋጭና አሳሳቢ ናቸው ሲሉ ዋና ዳይሪክተሩ ከ ኤ ኤፍ ፒ  ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ተናግረዋል፡፡

“በሰብአዊ ተቋማት ውስጥ ለሁለት አስርት አመታት  በስራ የነበረኝ ቆይታ ላይ እንደዚ አይነት አስደንጋጭ ሪፖርት ሰምቼ አላቅም” ማርዲን፡፡

“አብዛኞቸሁ በሰብአዊ አርዳታ ዙርያ ሚሰሩ የስራ ባልደረቦቼ እኔ የተሰማኝ ስሜት ነው የሚሰማቸው” ዳይሬክተሩ፡፡

ይህ የሴቶች ጥቃት  ቅድምያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው፤ ዳግም እንዳይደገም ሁላችንም ልንከላከለው ይገባል፤ እንዲሁም ተጠቂዎች ልናግዛቸው ይገባል ብለዋል፡፡

አምስት ወር ያስቆጠረዉ የትግራይ ጦርነት የሴቶች ፆታዊ ጥቃት የየእለት ተግባር ሆኖዋል ፡፡ ማርዲን በትግራይ ክልል የሚገኙት ዶክተሮችና ነርሶች እንደሚሉት ከሆነ አብዛኞች ፆታዊ ጥቃቶች የደረሰባቸው ሴቶች በኤርትራና በኢትዮጵያ ወታደሮች እንደተደፈሩ ነው ሚገልፁት፡፡

እንዲሁም በዚ ሳምነት አል-ጂዝራ በድረገፁ ያስነበበው ፁሁፍ ቡዝዋች አስደንግጠዋል፡፡ ፆታዊ ጥቃት ከደረሰባቸው ሴቶች በብዛት በወታደሮች ከተደፈሩ ብኋላ ማህጸናቸው በክብሪት በጋለ ብረት የተቃጠሉ ይገኙበታል፡፡ ምናልባት ከተቃጠሉ እድለኛ የሆኑ ሴቶች ናቸው ከሞት ተርፎ በሆስፒታሎች እንክብካቤ እየተደረገላቸው ያሉት፡፡

የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ማርክ ሎኮክ በሳለፍናቸው ሳምንታት ለፀጥታው ምክርቤት መንግስት በትግራይ ክልል ፆታዊ ጥቃቶች እንደ እንድ የጦር መሳርያ እየተጠቀመው እንደሆነ መግለፃቸውም ይታወሳል፡፡

የሁለቱም ሃገራት መንግስት በትግራይ የተደረገ ጦርነት የኤርትራ ወታደሮች መሳተፋቸው ክዶ ቢቆዩም በመጋቢት ወር ላይ ጠ/ሚ  ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ለተወካዮች  ምክርቤት  የኤርትራ ወታደሮች በጦርነቱ ላይ እንደተሳተፉ መግለፃቸውም ይታወሳል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኤርትራ አምባሳደር ለተባበሩት መንግስታት አምባሰደር ሶፍያ ተስፋማርያም ለጸጥታው ምክርቤት በፃፉት ደብዳቤ ላይ ኤርትራ ለመጀመርያ ግዜ ወታደርችዋ በትግረይ ጦርነት ላይ መሳተፋቸው አምና በአስቸኳይ ከትግራይ እንደሚለቁ ቢገልፅም እስካሁን ግን ምንም የተባለ ነገር የለም፡፡

የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ እያደረሱት ያሉ ሰቆቋ አሁንም እንደቀጠለ የተባባሩት መንግስታት የጸጥታ ምክርቤት ጨምሮ ብዙ አለማቀፍ ተቋማት እየገለፁ ነው እንዲሁም በጣም እንዳሳሰባቸው አየገለጹ ነው፡፡

በተጨማሪም ማርዲን እንዳሉት ከሆነ የዜጎች መፈናቀል እንደቀጠለ ነው ጦርነቱ ከተጀመር በአምስት ወር ውስጥ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ከመኖርያቸው ተፈናቅለዋል ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ እንዳሉት ከሆነ የአለማቀፍ ቀይ መስቀል ማህበረሰብ በትግራይ ክልል ጦርነት የተጎዱ ዜጎች ሲረዳ ቆይተዋል እሁንም ደጋፉ አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ናግረዋል፡፡

ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር የተለያዩ የሆስፒታል ተቋማት ከ500 በላይ ሴቶች መደፈራቸው ሪፖርት አድርጎ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ የሚገኘው ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሓየሎም ከበደ ከጦርነቱ በኃላ በዋና ዋና ሆስታሎች 829 ሴቶች መደፈራቸው ሪፖርት አድርገዋል ሲሉ ለአል ጂዝራ ገልጾ እንደነበር ሚዘነጋ አይደለም፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 15 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ