የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ም/ሊቀመንበርና የፋይናንስ ክፍል ሀላፊ በሰሜን እዝ ወታደሮች ተወሰዱ

0
568

በትግራይ ክልል ከነበሩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች አንድ የሆነዉ የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሳወት ምክትል ሊቀመንበር አቶ አሉላ ሀይሉና የፓርቲዉ የፋይናንስ ክፍል አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ካሕሳይ ሀይሉ  ዛሬ በመቐለ ከተማ በሰሜን እዝ ወታደሮች ወደ ሰሜን እዝ የወታደሮች ካምፕ እንደተወሰዱ የሳወት ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ሀያሉ ጎዲፋይ ለአዉሎ ሚድያ ተናግረዋል፡፡

ዛሬ ከቀኑ 7 ሰአት በመቐለ ከተማ አክሱም ሆቴል አካባቢ ከጓደኞቻቸዉ ጋር ሆነዉ ሻይ ቡና እያሉ በነበሩበት ወቅት የሰሜን እዝ ወታደሮች አቶ አሉላ ሀይሉንና አቶ ካሕሳይ ሀይሉን ለይተዉ ወደ ሰሜን እዝ የወታደሮች ካምፕ እንደወሰዷቸዉ ነዉ አቶ ሀያሉ የነገሩን፡፡

“ሊቀ መንበሩ እንደነገሩን እስካሁን ለምን ምክንያት ሁለቱም አባላቶቻቸዉ እንደወሰዷቸዉ የሚታወቅ ነገር የለም” ብለዋል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 14 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ