የመራጮች ምዝገባ እንደሚራዘም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ

0
260

ተጨማሪው ቀን ምን ያክል እንደሚሆን ቦርዱ ተወያይቶ እንደሚወስን ወ/ት ብርትኳን ገልጸዋል፡፡

የምርጫውን ሂደት በሚመለከት ጠ/ሚ ዐቢይ ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ጋር ተወያይተዋል

በምርጫው ሂደት አስካሁን የነበሩትን ክንውኖች በሚመለከት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ ላይ “የኢትዮጵያ ጠላቶች ምርጫውን ለማስተጓጎል፣ ደካማና የሚያዙት መንግስት ለመፍጠር ሌት ተቀን እየሰሩ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል” ብለዋል።

የዘንድሮው 6ኛው ብሔራዊ ምርጫ “ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ እንዲሆን በቁርጠኝነት እየሠራን ነው” ሲሉም ገልጸዋል

በውይይቱ ላይ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች በምርጫው ሂደት የእስካሁኑን ክንውን ሪፖርት አቅርበዋል።

በእስካሁኑ ሂደት የመራጮች ምዝገባ ተሳትፎ በጥሩ ሁኔታ የተከናወነባቸው ክልሎች መኖራቸው ተመልክቷል።

በሲዳማና ኦሮሚያ ክልሎች እንዲሁም ድሬዳዋና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሮች የመራጮች ምዝገባ “ከ80 በመቶ በላይ” አፈፃፀም መኖሩን አብራርተዋል።

በሌሎች ክልሎችም የመራጮች ምዝግባ አፈፃፀም ከ50 በመቶ በላይ መሆኑን ገልጸዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የመራጮች ምዝገባ እንደሚራዘም ጠቁመዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው ተጨማሪው ቀን ምን ያክል እንደሚሆን ግን ቦርዱ ተወያይቶ የሚወስን እና የሚያሳውቅ መሆኑን ሰብሳቢዋ ገልጸዋል።

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 14 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ