አራት ሆነዉ ከደፈርዋት በኃላ ማህፀንዋን በጋለ ብረት አቃጠልዋት – አል ጂዝራ

0
352

በህውሓትና ፌደራል መንግስት መካከል በተጀመረ ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ተወላጆች ከሚኖሩበት ቦታ ተፈናቅለዉ ወደ ሱዳን እንዲ ሰደዱ ምክንያት ሁነዋል፡፡

እንዲሁም ጦርነቱ ለብዙ ሴቶች መደፈር ምክንያት ሆነዋል፡፡ ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር የተለያዩ የሆስፒታል ተቋማት ከ500 በላይ ሴቶች መደፈራቸው ሪፖርት አድርጎ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ የሚገኘው ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሓየሎም ከበደ ከጦርነቱ በኃላ በዋና ዋና ሆስታሎች 829 ሴቶች መደፈራቸው ሪፖርት አድርገዋል ሲሉ ለአል ጂዝራ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት አሁንም እየቀጠለ እንደሆነ ብዙ አመላካች ነገሮች አሉ፡፡

የአማራ ክልል ልዩ ኃይል በጦርነቱ ተሳትፈዋል ሲል መንግስት በራሱ የሚድያ አውታሮች ሲነገር ቢደመጥም ስላደረሱት ጥፋት ግን ምንም ማለት አልቻለም፡፡

ከዚህ ቀደም የአማራ ክልል ኃይሎች በትግራይ ክልል በንፁኃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ሰቆቃ እና የሴቶች ፆታዊ ጥቃቶች እንዲቆም እንዲሁም ከክልሉ ለቆ እንዲወጣ የተለያዩ አለማቀፍ ድርጅቶች ተመድን ጨምሮ  የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቲር አንቶንዮ ብሎንከን መናገራቸው ሚዘነጋ ጉዳይ አይደለም፡፡

የአማራ ኃይሎች በትግራይ ክልል ለአማራ ክልል አዋሳኝ የሆኑ ቦታዎች ሑመራ፤ ወለቃይት የመሳሰሉ ቦታዎች ላይ ፆታዊ ጥቃቶች መፈፀማቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅት (ኢሳማኮ) ከዚህ በፊት መግለፁም ይታወሳል፡፡

ጥቃት ከደረሰባቸው ሴቶች ምስክርነታቸው ለአል ጂዝራ ከተናገሩ ሴቶች መካከል አንድዋ አክበረት ትባላለች፡፡ የ34 እድሜ ስትሆን እንዲሁም የሶስት ልጅ እናት ናት፡፡ አክበረት ከቤትዋ በወታደሮች ነው ተገድጄ የወጣሁት እንዲሁም ምንም እቃ እንድንይዝም አልፈቀድሉንም ትላለች ፡፡

የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም. ጥዋት ላይ የስድስት ወር ህፃን ልጅዋ በጀርባዋ አዝላ እንዲሁም የአራትና፤ሰባት አመት ልጆችዋ እና 14 እደሜ የሚሆነው ወንድምዋ በእጅዋ እየጎተተች በእግርዋ መጓዝ ጀመረች፡፡ 7 ስዓታት ከተጓዘች በኃላ ተከዘ ወንዝ ድልድይ ላይ ስትደርስ የአማራ ኃይሎች አክበረት ከልጆችዋ በመለየት ሰው የሌለው የገበሬ ቤቶች ውስጥ በማስገባት ለአራት ደፈርዋት፡፡ አክበረት ከደፈርዋት በኃላ “ብረት አግሎ ማህፀንዋን አቃጠሉኝ” ትላለች አክበረት፡፡

ደርጊቱን እንዲያቆሙት ለምኛቸው ነበር አክበረት ለአል ጄዝራ ስትናገር ይህን ለምን በኔ ላይ ሊያደርጉት እንደፈለጉ ጠየቅኳቸው “ምን አድርጊያቹ ነው”?

“አንቺ ለኛ ምንም አላረግሽንም” እንዳሏትና “የኛ ችግር ከማህፀንሽ ጋር ነው ምክንያቱም ማህፀንሽ ወያኔ ነው ሚወልደው ስለዚህ የትግራይ ማህፀን በፍፅም ልጅ መውለድ የለባትም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አኽበረት ማህፀንዋ በጋለ ብረት ካቃጠልዋት በኃላ ትትዋት ሄዱ፡፡ የ 14 እደሜ ያለው ወንድምዋ ጨምሮ ሌሎች ቦቦታው የነበሩ ተፈናቃዮች ከነበረችበት ቦታው አንስተዉ ወደ ሆስፒታል ወሰድዋት፡፡

በአክበረት ላይ የደረሰው ፆታዊ ጥቃት ዳግም እንዳትወልድ አድርጓታል፡፡ በህክምና ላይ የሚከታተላት ዶክተር ለአል ጂዝራ እንደተናገረው ከሆነ ከሰውነትዋ የሚፈስ ደም ማቆምያ የለውም፤ ለብቻዋ ተለይታ ነው እየተስተናገደች ያለችው፤ የደረሰባት ጥቃት ከባድ በመሆኑ መራመድ አትችልም፤ እንዲሁም በማታ ለመተኛት በጣም እያስቸገራት መሆኑ ዶክተሩ አክሎ ገልፀዋል፡፡

አክበረት ላይ የደረሰባ ፆታዊ ጥቃት መልኩ ቢቀይርም በሌሎች ብዙ ሴቶችም ደርሰዋል ሲል ዶክተሩ ለአል ጂዝራ ገልጽዋል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 14 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ