“ግብጽ እና ሱዳን በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን ድርድር ሊያከብሩ ይገባል” ኢትዮጵያ ለተመድ በጻፈችው ደብዳቤ

0
187
DCIM100MEDIADJI_0644.JPG

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ስለሚመራው የሶስትዮሽ ድርድር ያላትን አቋም ለተመድ የጸጥታው ም/ቤት በደብዳቤው አሳውቃለች፡፡

ግብጽ እና ሱዳን “የድርድሩን ሂደት በማኮላሸትና አለምአቀፋዊ በማድረግ ጫና ማሳደርን መርጠዋል”ም ነው ኢትዮጵያ በደብዳቤው ያለችው

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት በሚመራው “የሶስትዮሽ ድርድር ላይ ያላትን የፀና አቋም” ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በጻፈችው ደብዳቤ አስታወቀች ፡፡

“ግብፅ እና ሱዳን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሙሌትና አስተዳደርን በማስመልክት ወደሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር እንዲመለሱ፤ እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የድርድር ሂደት እንዲያከብሩ ሊያስስቧቸው ይገባል” ስትል ጥሪ አቅርባለች ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለወቅቱ የም/ቤቱ ፕሬዝዳንት በላኩት ደብዳቤ “በአፍሪካ ህብረት የሚመራው ሂደት የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም / ቤት የተሟላ ድጋፍ ያለው፣ መርሆዎችን መሠረት ያደረገና በአፍሪካ ላይ ለሚፈጠሩ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን በማፈላለግ መንፈስ የተቃኘ” መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል ጥልቅ ፍላጎት ቢኖርም ፤ግብፅ እና ሱዳን ሁሉንም ሀገራት ተጠቃሚ ወደሚያደርገው መፍትሄ ለመምጣት በሚያስችል ቅን ልቦና እየተደራደሩ እንዳይደለም ነው አቶ ደመቀ በደብዳቤው የጠቀሱት፡፡

ሃገራቱ ድርድሩን “በማኮላሸት” እና ጉዳዩን “ዓለም አቀፍ በማድረግ” በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደርን መምረጣቸውንም ነው የገለፁት፡፡

ደብዳቤው ኢትዮጵያ በህብረቱ በሚመራው የሶስትዮሽ ድርድር የማይናወጥ ቁርጠኝነት እና እምነት እንዳላት ያስረግጣል፡፡

ደቡብ አፍሪካ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጉዳዩን ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ በሚለው መርህ ለመፍታት ላደረጉት ያላሰለሰ ጥረት ያላትን አድናቆትም ገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ የግድቡ ሁለተኛ ዙር ሙሌት በመጪው ክረምት ከመፈጸሙ በፊት መረጃ ለመለዋወጥ ያደረገችውን ጥረትም አስታውሷል ምንም እንኳን ጠይረቷን ሁለቱም የታችኞቹ የተፋሰሱ ሃገራት ባይቀበሉትም፡፡

ሃገራቱ በአስገዳጅ ስምምነት ስም ኢ-ፍትሐዊ ሁኔታዎችን ለማስጠበቅ እና በግድቡ ውሃ እንዳትጠቀም ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት ተቀባይነት እንደሌለውም ኢትዮጵያ በደብዳቤው አስታውቃለች አል ዐይን ዘግቧታል፡፡

ይህ እንዲህ እንዳለ የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ “የታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድር የደረሰበትን ደረጃ ለማስረዳት” ያለመ ነው የተባለለትን፤ በስድስት የአፍሪካ አገሮች የሚያደርጉትን ጉብኝት ትላንት ጀምርዋል። ሳሜህ ሽኩሪ ከሚጎበኟቸው አገራት መካከል ድርድሩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ደቡብ አፍሪካ ይገኙበታል።

የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አሕመድ ሐፌዝ የሽኩሪ ጉዞ “ድርድሩ ያለበትን ትክክለኛ ደረጃ ለአፍሪካ አገሮች ለማስረዳት እና ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ሳይጀመር አስገዳጅ ህጋዊ ስምምነት ላይ የሚደረስበትን መንገድ ለመደገፍ” ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

እንዲሁም የሶስቱ ሃገራት መሪዎች እ.ኤ.አ በ2015 በሱዳን ካርቱም ለፈረሙት የመርሆዎች ስምምነት ያላትን ቁርጠኝነትም ገልጻለች ግብጽ እና ሱዳን በስምምነቱ የገቡትን ቃል አለመጠበቃቸውን በመጠቆም፡፡

ከዚህ ውጭ ጫና ለማድረግ የሚደረጉ የትኛውም ዓይነት ሙከራዎች እና ድርድሩን ከህብረቱ ውጭ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶች በሃገራቱ መካከል ያለውን መተማመን የበለጠ እንደሚጎዱ ነው ኢትዮጵያ በደብዳቤው የገለጸችው፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 12 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ