የቻድ ፕሬዚዳንት ምርጫ አሸንፈዋል በተባሉ በሰዓታት ልዩነት ተገደሉ

0
292

ላለፉት 30 ዓመታት ቻድን የመሩት ፕሬዝደንት ኢድሪስ ዴቢ በአማጺ ኃይሎች መገደላቸውን የሀገሪቱ መከላከያ ማስታወቁን ተገለጸ፡፡

ፕሬዝደንቱ የመንግስት ኃይሎች ከአማጺያን ጋር እያደረጉ ባለው ጦርነት ተመተው መገደላቸውን ነው መከላከያ ሠራዊቱ በሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ይፋ ያደረገው፡፡

ፕሬዝደንቱ በውጊያው ከቆሰሉ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ነው ህይወታቸው ያለፈው፡፡

ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ ፣ በቻድ ምርጫ እስካሁን ከተቆጠረው 80 በመቶ ድምጽ ከ79 በመቶ የሚሆነውን በማግኘት ማሸነፋቸው በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኖ ነበር፡፡

የቻድ አማጺያን በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ዋና ከተማዋ ኒጃሚና ከትናንት ጀምሮ በመቅረብ ላይ እንደነበሩ የሚገልጹ መረጃዎች ወጥተው ነበር፡፡

የቻድ አማጺያን በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ዋና ከተማዋ ኒጃሚና ከትናንት ጀምሮ በመቅረብ ላይ እንደነበሩ የሚገልጹ መረጃዎች ወጥተው ነበር፡፡

አማጺያኑ ወደ ዋና ከተማዋ ኒጃሚና መጠጋታቸውን ተከትሎ በሀገሪቱ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ዲፕሎማቶች ሀገሪቱን እንዲለቁ የአሜሪካ መንግስት በትናንትናው ዕለት ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር፡፡

አማጺያኑ ወደ ዋና ከተማው እንቅስቃሴ ማድረግ የጀመሩት በቻድ የተካሄደውን ምርጫ ፕሬዘዳንት እድሪስ ዴቢ ለሶስተኛ ዙር የስልጣን ዘመን መምራት ከጀመሩ በኋላ ነው፡፡ በፈረንጆቹ 1990 ስልጣን የተቆናጠጡት ዴቢይ እስላማዊ ታጣቂዎችን በመዋጋት የፈረንሳይና የአሜሪካ ዋነኛ አጋር ናቸው፡፡

አማጺያኑ ወደ ዋና ከተማዋ ኒጃሚና በመቅረባቸውና የጸጥታ ችግር ይኖራል በሚል ስጋት ምክንያት፣ የአሜሪካ ኢምባሲ ሰራተኞች በመንገደኞች አውሮፕላን ቻድን እንዲለቁ መታዘዛቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ዋቢ አድርጎ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የብሪታኒያ መንግስትም እንዲሁ የቻድ አማጺያንን የያዙ ሁለት ተሽከርካሪዎች ወደ ዋና ከተማዋ በመቃረባቸው ምክንያት ዜጎቹ ከሀገር እንዲወጡ አሳስቧል፡፡

ከባድ መሳሪያ የታጠቁ የቻድ የጸጥታ ሀይሎች በዋና ከተማዋ ሲዘዋወሩ እንደነበር ሮይተርስ የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 12 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ