በአማራ ክልል ትላንት የጀመረው የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬም እንደቀጠለ ነው

0
294

ከትላንት ጀምሮ በአማራ ክልል በተለያዩ ቦታዎች የብልፅግና አስተዳደርን የሚቃወሙ ህዝባዊ ተቃውሞ እንደ ቀጠሉ ነው፡፡

ሰልፎቹ በአማራ ክልል ወልዲያ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ባሕር ዳር፣ ሐይቅ፣ ሰቆጣ “የአማራ ግድያ በቃ” የሚል መፈክር ይዞ መውጣታቸው ታይተዋል፡፡

በሌላ በኩል በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎችም የተቃውሞ ድምፃቸውን ለማሰማት የምግብ አድማ በማድረግ የሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።

በትላንተናው እለት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲና በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች የንፁሃን ግድያና ሞት ይብቃ በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል።

በሰልፉ የሚሳተፈው የማህበረሰብ ክፍል ከፍተኛ ሲሆን የንፁሃን ሞት ይብቃ የሚሉና አስተዳድራዊና መንግስታዊ ብሎም መዋቅራዊ በደሎች እንዲቆሙ የሚጠይቁ መፈክሮች የታዩበት ነው።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣየ ከተማ ካራ ቆሬና ሸዋሮቢት እንዲሁም ከሚሴና አካባቢው በርካቶች የተገደሉ ሲሆን ከተሞችም ወድመዋል።

ይህንን ተከትሎ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን በትላንቱ ናው አልት ህዝባዊ ትግል እንዲካሔድ ጥሪ አቅርቧል።

በክልሉ የተለያዩ ከተሞች በተካሄዱት እና በርካቶች በተሳተፉባቸው ሰልፎች ማንነትን መሰረት ያደረገው ግድያ እና ሞት መፈናቀሉም ጭምር ተወግዟል፡፡

በሰልፎቹ ድርጊቱን ከማውገዝም ባሻገር እንዲቆም ወንጀለኞችም ለህግ እንዲቀርቡ የሚያጠይቁ መልክዕቶች ተንጸባርቀዋል፡፡

ተቃውሞ ሰልፎቹ በክልሉ ሰሜን ሸዋ ያጋጠመውን ሰሞነኛ ሞትና መፈናቀል ተከትሎ የተደረጉ ናቸው፡፡

ሰልፎቹ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ ህዝባዊትግል ያስፈልጋል ትግሉንም ከፊት ሆኘ እመራዋለሁ ያለው የአማራ ብሔራዊንቅናቄ አብን መግለጫን ተከትሎ ነው እየተካሔዱ ያሉት።

ነገር ግን ሰልፎቹን ማን እንደሚያስተባብራቸውና በማን እንደሚመሩ በይፋ የታወቀ ነገር የለም ብሏል የክልሉ መንግስት። ሆኖም በወልዲያ የተካሄደው ሰልፍ በአማራ ወጣቶች ነፃ ማህበር አስተባባሪነት መካሄዱን የከተማው ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በክልሉ ሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አጎራባች በሆኑ የኤፍራታ እና ግድም፣ የአንጾኪያ እና ገምዛ እንዲሁም የቀወት ወረዳ አካባቢዎች ባጋጠመው ሰሞንኛ የጸጥታ ችግር በርካቶች ህይወታቸውን አጥተዋል፤ የመኖሪያ ቀያቸውንም ለቀው ተሰደዋል፡፡

ሆኖም አሁን በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ተከትሎ የሸዋሮቢት እና የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ መኖሪያቸው እየተመለሱ ነው ተብሏል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን እና የአማራ ክልል ባለስልጣናት ጥቃቱን “የኦነግ ሸኔ የጥፋት ኃይል ነው ያስፈጸመውና ያስተባበረው” ማለታቸውን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል፡፡

መከላከያ ሚኒስቴር ችግሩ ባጋጠመባቸው የሰሜን ሸዋ፣የቡብ ወሎ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የክልል እና የፌዴራል የጸጥታ ተቋማትን ያካተተ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን ማስታወቁ የሚታወስ ነው።

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 12 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ