በትግራይ በጦርነት ምክንያት1.4 ሚሊዮን ተማሪዎች ከት/ቤት ገበታቸው ቀርተዋል ተባለ

0
130

በትግራይ ክልል ዉስጥ በህውሓት እና ፈደራል መንግስት በተጀመረ ጦርነት 1.4 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ቀርተዋል ተብለዋል፡፡

ኤዱኬሽን ካኖት ወይት የተባለው አንድ የገብረ ሰናይ ድርጀት በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ ክልል ከትምህርት ገበታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች አንድ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለግሰዋል፡፡

እርዳታው ለ20 ሺ ሚያክል ተማሪዎች እንዲሁም በጦርነቱ ምክንያት ለተጎዱ ተማሪዎች ሲሆን ለ12 ወር የሚቆይ እንዲሁም በዩኒሴፍ፤ ትምህርት ሚኒስትር ፤ በሴቭ ዘ ችልድረን እና በሲቪል ማህበረሰብ ተፈፃሚ የሚሆን ነው ተብለዋል፡፡

እርዳታው ያለመው ለ2ሺ ለመዋእለ ህፃናት፣ 12ሺ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች፤ 6ሺ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና 250 አስተማሪዎችን ያጠቃልል ተብለዋል፡፡

የእርዳታው 52 በመቶ ተደራሽ የሚሆነው ለሴቶች ሲሆን 10 በመቶ ደግሞ ለአካል ጉዳተኛ ህፃናት ነው የተባለው፡፡

በትግራይ ክልል ጦርነቱ ከጀመረ ጀምሮ ብዛት ያለቸው ህዝብ የሚያገለግሉ የት/ቤት ተቋማት መውደማቸው የተለያዩ ተቋማት መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

ሆኖም የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ጌትነት መኩርያ እንዳሉት ከሆነ በክልሉ በጦርነት የወደሙ የት/ቤቶች መሰረተ ልማት ለመጠገን መንግስት 3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መመደቡ ገልፆ የትም ቢሆን ት/ቤቶች መጠበቅ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 12 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ