ኢንሳ በ2.5 ቢሊዮን ብር አዲስ ያስገነባው የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ተመረቀ

0
90

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በ2.5 ቢሊዮን ብር አዲስ ያስገነባው የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል።

በአዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አካባቢ 23 ሺህ 371 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ሕንፃው ከ14-17 ወለል ያላቸው 5 ብሎኮችን የያዘ ሲሆን ግንባታው በ2002 ዓ.ም የተጀመረ ነው።

ሕንፃዎቹ በውስጣቸው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን ጨምሮ የሰላም ሚኒስቴር፣ የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማእከልን እና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማእከልን ያካትታሉ።

ተቋሙ በየዓመቱ ለቢሮ ኪራይ ያወጣ የነበረውን 87 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚያስቀርም ተገልጿል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ቢሮዎች፣ የምርምር ማእከሎችን፣ ላብራቶሪዎችን እንዲሁም ከ7 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ያሉ ባለልዩ ተሰጥኦ ታዳጊዎች የምርምር ሥራ የሚያከናውኑበት የሳይበር ልማት ማእከልን በውስጡ ይዟል ሲል ኢቢሲ ዘግቧታል።

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 09 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ