ኮቪድ – 19 ሰላሳ ሚሊዮን አፍሪቃውያንን ወደ ድህነት እያስገባ ነው – አይኤምኤፍ

0
116

ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪቃ አገራት ውስጥ ከ30 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ወደ ድህነት እንደሚገቡ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) አስጠቅቋል ፡፡

ድርጅቱ የአፍሪቃ አገራት የተሻለ ክትባት እንዲያገኙ የበለፀጉ አገራት እንዲረዱ ጥሪ አቅርቧል እንድ ቢቢሲ አፍሪቃ ዘግባ፡፡

አይ ኤምኤፍ እንደገመተው አንዳንድ የአፍሪቃ አገራት 60 በመቶውን ህዝባቸውን ክትባት ለመከተብ እንዲቻላችው የጤና ወጪዎቻቸውን በ50 በመቶ ከፍ ማድረግ ያስፈልጋቸዋል ፡፡

ባለፈው ዓመት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪቃ አገራት ኢኮኖሚያቸው በ 2 በመቶ ገደማ ቀንሷል ፡፡ የእንቅስቅሴ ገድቦች የንግድ ድርጅቶችን ጎድተዋል፣ ከገበያ፣ መሸጫ ባለቤቶች እስከ ቱሪስት መዝናኛዎች ፡፡

የወጣት ቁጥር መኖሩ አህጉሪቱን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የረዳ ይመስላል የሚለው ድርጅቱ ፡፡

ይሁን እንጂ የአፍሪቃ ህዝብ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ በመምጣቱ እጅግ በጣም ብዙ ወጣቶች ሥራ ይፈልጋሉ ተብሏል፡፡

ስለዚህም የእንቅስቅሴ ገድቦች  በተቻለ ፍጥነት መነሳት አለባቸው ደግሞም በመላው አህጉር ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖን ለመቀነስ ክትባቱ በፍጥነት መሰጠት እንዳለበት ተገልጸዋል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 08 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ