በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በድጋሚ ግጭት ተከሰተ

0
346

በሁለቱ ዞኖች ከአንድ ወር በፊት በተነሳ ግጭት ከ300 በላይ ሰዎች ህይወት ስለማለፉ መገለጹ ይታወሳል እነዲሁም ግጭቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የክልሉ ልዩ ሀይል እና መከላከያ ሰራዊት ተሰማርቶ ለጊዜው ግጭቱ ቆሞ ነበር።

ይሁንና በአጣዬ ከተማ ከትናንት በስቲያ አንድ መኖሪያ ቤት መቃጠሉን መነሻ በማድረግ በአካባቢው ውጥረት ነግሶ ከዛሬ ሌሊት አንስቶ ግጭቱ ተከስቶ የሰዎች ህይወት በማለፍ ላይ መሆኑን ለአል አይን ዜና ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ እንዳሉት ትናንት ጀምሮ በኤፍራታ እና ግድም ቀወት እና ወረዳ እና በአንጻኪያ ወረዳ ስር ባሉ ካራቆሬ ቆሪሜዳ ማጀቴ መስኖ ካብሰራምባ ገተም ውሃ ኩሪብሪ ዋጮ እና ዘንቦ ቀበሌዎች ግጭት ተከስቶባቸዋል።

ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ በአጣዬ ከተማ ከባድ የተኩስ ልውውጥ በመደረግ ላይ መሆኑን የተናገሩት ነዋሪዎቹ ችግሩ በአካባቢው ካለው ልዩ ሀይል እና መከላከያ ሰራዊት አቅም በላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ወደነዚህ ቀበሌዎች በመግባት ጥቃት በመፈጸም ላይ ያሉት ታጣቂዎቹ የያዙት የጦር መሳሪያ ዘመናዊ ከመሆኑ የተነሳ ታጣቂዎቹ ወደ መከላከያ ሰራዊት ላይም እየተኮሱ መሆኑንም ገናዋሪዎቹ ተናግረዋል።

ጥቃቱ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያትም ነዋሪዎቹ አሁን ላይ መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው ወደ ሌሎች አጎራባች ቀበሌዎች እና ከተሞች በመሸሽ ላይ መሆናቸውንም አክለው ተናግረዋል።

በግጭቱ ምክንያት ከአዲስ አበባ- ደሴ -መቐለ የሚያስኬደው ዋና መንገድ ትራንስፖርት መቋረጡንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

ከአዲስ አበባ እና በሰሜን ሸዋ ዞን ስር ካሉ ከተሞች ወደ ከሚሴ አጣዬ ኮምቦልቻ ደሴ እና መቐለ ለመጓዝ መንገድ የጀመሩ የጭነት እና የህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ሸዋሮቢት ላይ መቆማቸው ተገልጿል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ሰላምና ደህንነት መምሪያ ሀላፊ አቶ አበራ መኮንን በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው ቢሆንም ያሉበት ሁኔታ መረጃ መስጠት የማያስችል አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ነግረውናል።

ከአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ብያደርግም አልተሳካም።

ሁለቱ ዞኖች ከአንድ ወር በፊት በተነሳ ግጭት ከ300 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ባወጣው ሪፖርት መግለጹ ይታወሳል ሲል አል ዐይን ዘግቧታል።

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 08 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ