ሶማሊያ በውስጥ ጉዳይዋ ጣልቃ የገቡ ኃይሎችን ተቸች

0
132

የሶማሊያ መንግሥት የፕሬዚዳንቱን የሥልጣን ማራዘሚያ ውሳኔ እንደጸና በመግለጽ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሀገሪቱን የዴሞክራሲ ሂደቶች ለማደናቀፍ እየፈለገ ነው ሲል በብርቱ ተችቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመግለጫው፣ ከአንዳንድ ዓለም አቀፍ አጋሮቻቸው በሰጡት መግለጫ መደናገጣቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህንን የእኛን ውሳኔ እኚህ ሀያላን ሀገራት  “በተሳሳተ መንገድ ተረድተውታል” ብሏል፡፡

የብሔራዊ ተቋማትን የፖለቲካ ነፃነት እና ሉዓላዊ መብቶች የሚሸረሽሩ በማስፈራራት የተሞሉ የብጥብጥ መግለጫዎች፣ በሶማሊያ ውስጥ አሸባሪ ድርጅቶችን እና ፀረ-ሰላም አካላትን  ለማበረታታት ብቻ ያገለግላሉ እንደሁን እንጂ ይህ ለእኛ አንዳችም ጥቅም የለውም ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡

ይህንን የፓርላማ ውሳኔ ዓለም አቀፍ አጋሮቻችን መደገፍ አለመቻላቸውም ብሏል፡፡

የሶማሊያ የታችኛው ምክር ቤት ሰኞ እለት የፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆን የስልጣን ዘመን እና የፌደራል ፓርላማውን ለሁለት ዓመታት ያህል  ማራዘሙ ይታወሳል እንደ፡፡

ይህንን ውሳኔ በሶማሊያ ተቃዋሚ መሪዎች እና በጅቡቲ እና በፑንትላንድ ክልላዊ መንግስታት እንዲሁም የሀገሪቱ ሴኔት ተችቷል ፡፡

የሶማሊያ ለጋሾች አሜሪካን እና የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ውሳኔውን ከፋፋይ እና የሀገሪቱን መረጋጋት አደጋ ላይ ይጥላል ሲሉ ተቃውመዋል፡፡

በውጤቱም ሁለቱም ከአገሪቱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንደገና እንደሚያጤኑ ተናግረዋል ሲል ቢቢሲ ተግቧታል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 07 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ