በትግራይ ክልል 19 ንፁሀን ዜጎች ጉዳት ደረሰባቸው ተባለ

0
344

የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል አድዋ ውስጥ ተኩስ በመክፈት በ19 ንፁሃን ዜጎች ላይ ጉዳት አድርስዋል ሲል በቦታው የነበሩ የአየን እማኝ ዶክተሮችን ጠቅሶ ኤ ኤፍ ፒ ዘግቧል።

ትላንት ማክሰኞ በቦታው የነበሩ ዶክተሮችን እማኝ አደርጎ የጠቀሰው ዘገባው ይህ ድርጊት የተፈፀመው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ መሬት ለቆ ይወጣሉ ካሉ ከሳምንታት በኃላ ነው።

እንዲሁም የ ቡድን 7 ሃገራት የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ይለቃሉ ብሎ ያቀረበው ሃሳብ በጥሩ ጎን እንደሚዩት ከገለፁ በኃላ የኤርትራ ወታደሮች 19 ንፁሃንን መጉዳታቸው ነው የተዘገበው።

“ገና በጥዋቱ የተኩስ ድምፅ ሰማን ፤ ትንሽ ሳይቆይ ወደ ሆስፒታል ተጠራን” ሲል በዓድዋ ሆስፒታል የሚሰራ ዶክተር የነበረው ሁኔታ ለ ኤ ኤፍ ፒ ተናግረዋል፡፡

ስሙን መግለፅ ያልፈለገው ዶክተር አክሎም ልክ ሆስፒታሉ ስንደርስ 19 ሰዎች በጥይት ተመትተው ነበር ፤ አስሮቹ በጠና የታመሙ ወይም የቆሰሉ ሲሆን አምስቶቹ ደግም መጠነኛ ጉዳት እንደ ደረሰባቸው ቀሪዎቹ አራቱ ቀላል ጉዳት ገጥሟቸዋል ብሏል።

ኤ ኤፍፒ የአይን እማኞች ነገሩኝ ብሎ እንደዘገው ከሆነ ጥቃቱ የተፈፀመው የባንክ ወረፋ ላይ እንዲሁም መንገድ ላይ ሲጓዙ የነበሩ ንፁሀን ላይ ነበር ብለዋል፡፡

ከዚ በፊት የነበረው ግድያ የኤርትራ ወታደሮች ከመኪና ወርደው ነበር ንፁሀን ዜጎች ላይ ጉዳት የሚደርሱት አሁን ግን ሁኔታው ተቀይረዋል ጥቃቶች የሚፈፀሙት በየቦታው ተበታትነው በመንገድ የሚልፉ ሰዎችን ሳይቀር ነው ብለዋል።

የዓድዋ ነዋሪዎች ለ ኤ ኤፍ ፒ እንደተናገሩት የኤርትራ ወታደሮች በለበሱት የወታራዊ ዩንፎርም እና የቋንቋ ቅላፅያቸው መለየት ይቻላል ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል ውስጥ የፈፀሙት ኢ ሰብአዊ ድርጊቶች እና በአክሱም ላይ የተደረጉ ጭፍጨፋዎች እንዲሁም የሴቶች መደፈር መንግስታቸው እንደካደ የሚታወቅ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስት ዐብይ አሕመድ አስመራ ድረስ በመሄድ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እንደሚወጡና ያጠፉት ጥፋት ካለም በመንግስታቸው ተጠያቂ እንደሚሆኑ በመጋቢት ወር ላይ ለተወካዮች ምክርቢት መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

ሁኖም ምን ያህል የኤርትራ ወታደሮች እንዳሉ እና መቼና እንዴት እነዚህ ወታደሮች ትግራይ ክልልን ለቀው እንደሚወጡ የታወቀ ነገር አልነበረም፡፡

ይህ የኤርትራ ወታደሮች በአድዋ የፈፀሙትነ ጥቃት ተከትሎ የአለም አቀፍ ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን (ኤም ኤስ ኤፍ) በትዊተር ገፁ እንዳሰፈረው ከሆነ 18 ቁስለኞች በአድዋ ሆስፒታሎች እንደደረሱ እና አስራ አንዱ ከፍኛ ጉዳት ደርሶባቸው አክሱም ከተማ ወደሚገነው ሆስፒታል ሪፈር ተብለዋል ሲል በትዊተር ገፁ ያሰፈረው ፅሁፍ ይገልፃል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 06 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ