ጅቡቲ በኢትዮጵያ ያለው አለመረጋጋት ኢኮኖሚየን አቃውሶብኛል አለች

0
147303

በኢትዮጰያ ያለው አለመረጋጋት ለጅቡቲ ትልቅ የኢኮኖሚ ድክመትን ፈጥረዋል ሲሉ የጅቡቲ የገንዘብ ሚኒትር አሊያያስ ዳዋሌህ ተናግረዋል።

የጅቡቲ ኢኮኖሚ ባለፈው አመት ከነበረበት ውድቀት በፍጥነት ሊያገግም የሚችለው በጎረቤት ሃገር ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ግጭት ሲያቆም ነው ሲሉ ከቅርብ ግዜ ወዲ በፍጥነት እየጨመረ የመጣው ግጭት ለቀጠናዊ ሰላም ፣ ለንግድ እንዲሁም ለክልላዊ ትብብር ተስፋ አስቆራጭ እየሆነ ነው ያሉት ዳዋሌ በብሉምበርግ ለተጠየቁት ጥያቄዎች በኢሜል በሰጡት ምላሽ በእነዚህ ውጫዊ እና ውስጣዊ ምክንያቶች ሳብያ የጅቡቲ ምጣኔ ሀብት በቅርቡ ላያገግም ይችላል ብለዋል ሚኒስትሩ አሌያያስ ዳውሌህ።

በሱዌዝ ቦይ መግቢያ ላይ የምትገኘው ጅቡቲ በአፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ የሕዝብ ብዛት ላላት ኢትዮጵያ ዋና የንግድ መተላለፊያ ናት ፡፡

ይህቺ ለጅቡቲ ዋና አጋር በሆነችው ኢትዮጵያ በፌድራል መንግስት እና በህወሓት በተጀመረው ጦርነት እንዲሁም የኮረና ቫይረስ ጫና ተጨምሮ የሃገሪትዋን ኢኮኖሚ አለመረጋጋት አሳይተዋል፡፡

የጅቡቲ ኢኮኖሚ በባለፈው አመት ከነበረበት 1% የቀነሰ ሲሆን በዚህ አመት ከነበረበት 5% ቀንሷል።

እንዲሁም የአለማቀፍ የገንዘብ ድረድጅት (አይ ኤም ኤፍ) በቀጣዩ 2022 የፈረንጆች የበጀት አመት የጅቡቲ ኢኮኖሚ በ5.5% ሊቀንስ እንደሚችል ተንብዩዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጅቡቲ በቀጣይ አመታት በወደብ፤ በአረንጓዴ ኃይል እና በቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንት በመጪው ዓመታት ከ 7% ወደ 9% ለማሳደግ ሂደት ላይ እንዳለች የሃገሪትዋ ገንዘብ ሚኒትር ዳዋሌህ ገልፀዋል፡፡

ሀገሪቱን ለሁለት አስርት ዓመታት ሲያሰተዳድሩ የቆዩት የ73 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ ጅቡቲ በቅርብ ባደረገችው ሃገራዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት ሆነው መሸነፍ ችለዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ሃገራቸው ጅቡቲ በኢኮኖሚ የላቀች ሃገር ለማድረግ ብዙ እቅድ እንዳላቸው ሲገልፁ ቆይተዋል። ሆኖም የጎረቤት ሃገራትን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከፍተኛ የጀቡቲ ወደብ ተጠቃሚዎች ላይ ዘላቂ ሰላም መኖር ለጅቡቲ ኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ እንደሆነ የገንዘብ ሚኒትሩ ገልጸዋል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 05 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ