ደቡብ ክልል በተወሰኑ አከባቢዎች የጸጥታ ችግር አለ ተባለ

0
147287

ደቡብ ክልል በተወሰኑ አከባቢዎች የጸጥታ ችግር ያለ ሲሆን በዋናነት 3 ስፍራዎች ላይ ችግሩ በስፋት ተስተውሏል ተብሏል፡፡

በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪና የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየው ባውዲ ለአሐዱ እንደገለጹት የሱርማ ብሄረሰብ አከባቢዎች፣ አማሮ ልዩ ወረዳና ጉራፈርዳ ወረዳ ችግር ያለባቸው አከባቢዎች ናቸው፡፡

ሱርማ አከባቢ ያሉ አርሶ አደሮች የታጠቁ በመሆናቸው ሰላም ለማስከበር ወደ ስፍራው ከገቡት ልዩ ኃይሎች መካከል 5ቱን ገድለው 7 የሚሆኑት ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት አድርሰዋል ሲሉ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

ግጭት ያለባቸው አከባቢዎች ሰላማዊ እንዲሆኑ ለማስቻል ከአዋሳኝ ድንበር አመራሮች ጋር በጋር በመሆን በፖለቲካዊ አካሄድና በህግ ማስከበር ዘርፍ የተቀናጀ ስራ ለመስራት መታቀዱን አቶ አለማየው ገልጸዋል፡፡

በየጫካው ያሉትን ሽፍቶች እጅ እንዲሰጡ ከማድረግ ጀምሮ ልዩ ኃይሎችን በማደራጀት ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ክልሉ ዝግጁ መሆኑን ኃላፊው ገልጸው ከህብረተሰቡ ጥቆማ እንዲሰጥና ከፍትህ አካላት ጋር ተናቦ እንዲሰራ ለማስቻል ውይይቶች እየተደረጉ ናቸው፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 05 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ