የግብፅ ዕጩ ፕሬዝዳንት የነበሩት ሃምዲን ሳባሂ ለህዳሴ ግድቡ ጦርነት ብቸኛ አማራጭ ነው አሉ

0
222

በታላቁ ህዳሴው ግድብ ዙርያ በሶስቱ ሃገራት የነበረው ድርድር አለመሳካቱ ተከትሎ ሀገራቸው ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ቀውስ ውስጥ የገባችባቸው በግብፅ ዕጩ ፕሬዝዳንት ሆነው ተወዳዳሪ የተበሩት ሃምዲን ሳባሂ መንግስታቸው ለጦርነት እንዲዘጋጅ ጥሪ አቀረቡ ሲል ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧታል፡፡

ሃምዲ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባወጡት ፅሁፍ መሰረት ህዝቡና ማህበረሰቡ እንዲሁም ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከር የሚሹ ሁሉ ለጦርነት አስቸኳይ እቅድ ማውጣት እንዳለባቸው ጥሪ እቅርበዋል፡፡

ፖለቲከኛው ኢትዮጵያ ግድቡን ከገደበች ግብፅ ማግኘት ያለባት የውሃ መጠን ሊቋረጥ ይችላል ብለዋል። ሀገራቸው ግብፅ ለጦርነት ትዘጋጅ ያሉት ፖለቲከኛው አንድነት በህዝቦች ብሎም በሰራዊቱና በህዝቦች መካከል በመፍጠር እንዲሁም የህሊና እስረኞችን በአስቸኳይ በመልቀቅና በማጠናከር ወደ ጦርነት መጓዝ ያስፈልጋል ብለዋል።

ሚዲል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ይህ እርምጃ የውጭ ሃይልን ለመቋቋም የውስጥ ቁስሎችን ይፈውሳል ብለዋል፡፡

በግድቡላይ የተደረገው ውይይትና ደርድር ለ10 ዓመታት ውድቀት አምጥቶብናል የሚሉት ፖለቲከኛው ለሁለተኛ ጊዜ የህዳሴው ግድብ ሙሌት ከመጀመሩ በፌት ግብፅን ለማዳን የቀሩት ከ80 ቀናት በታች እንደሆኑ ሳባሂ ጠቁመዋል፡፡ ይህ ለግብፅና ለመንግስት የህልውና ስጋት ነውና የጦርነት ድል ብቸኛ አማራጭነው ብልዋል፡፡

በግብፅ የሀገራቸው መንበር የናፈቃቸውና የሀገራቸውን የስልጣን መንበር በአንባገነት ተቆናጠው መዝለቅ የፈለጉ ፖለቲከኞች በኢትዮጵያላይ ጦርነት እንክፈት ማለት ከጀመሩ አስር አመታት ተቆጥረዋል።

የግብፅ ፖለቲከኞች የህዳሴ ግድቡን እንዳይገደብ ለማድረግና የኢትዮጵያ መለወጥ በማደናቀፍ ለዘመናት የተጓዙበት መንገድ በድርድርና በዲፕሎማሲ ለማስቀጠል እየጣሩ ቢሆንም ክሽፈትና ዝንፈት እየገጠመው ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በግብፅ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ትላንት ሰኞ ከግብፁ አቻቸው ሳሚ ሹክሪ ጋር በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ይታወሳል፡፡

የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመግለጫው ወቅት ፣ ከሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ በግብፅ ፣ በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል “የሁሉም ወገኖች ጥቅም የሚረጋገጥበት ስምምነት መደረስ አለበት” ብለዋል፡፡

ሩሲያ በድርድሩ ቴክኒካዊ ድጋፍ ለማድረግ ሀሳብ አቅርባ እንደነበር ያስታወሱት ሚስተር ላቭሮቭ ፣ ይሁንና በተደራዳሪ ሀገራት መልስ እንዳልተሰጣት ነው ያነሱት፡፡ “የአፍሪካ ሕብረት የሕዳሴ ግድብን ችግር መፍታት አለበት” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹክሪ በበኩላቸው “በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በመተማመን ላይ ነን” ብለዋል፡፡

ከግድቡ ጋር ያለውን አለመግባባት ሩሲያ መገንዘቧን የገለጹት ሚኒስትሩ ፣ ሩሲያ በግድቡ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ወሳኝ ሚና መጫወት እንዳለባትም ነው የተናገሩት፡፡

ያም ሆነ ይህ ኢትዮጵያ በመጪው ክረምት የግድቡን ሁለተኛ ዙር ሙሌት እንደምታከናውን በያዘችው አቋም ፀንታ የቀጠለች ሲሆን የግብፅ መሪዎችም በኢትዮጵያ ላይ ዛቻቸውን ቀጥለዋል::

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 05 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ