የ90 ዓመቷ ጃፓናዊት የዓለማች አንጋፋ ስራ እስኪያጅ በመሆን ሪከርድ ሰበሩ

0
51

በዚህ ዘመን ሽምግልናን እንደ እድል የቆጠሩ በርካታ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን ያለፉት ጃፓናዊት ሪከርድ ሰብረዋል።

በተለይም ኮሮና ቫይረስ በርካታ እድሜ ጠገቦችን በማጥቃቱ በርካቶች ከሞት ለማምለጥ ቤት ውስጥ መዋል በጀመሩበት በዚህ ዓመት የ90 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ስራ አስኪያጅ ሆነው እያገለገሉ ነው።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1956 ጀምሮ በአንድ ኩባንያ ውስጥ የሰሩት የ90 ዐመቷ ጃፓናዊት አዛውንት በዓለም አንጋፋዋ የቢሮ ስራ አስኪያጅ በመሆን ጊነስ ወርልድ ሪኮርድ ሰበሩ፡፡

የ 91 ልደታቸው ግንቦት 07/ 2013 ሚያከብሩት የሱኮ ታማኪ በሳምንት አምስት ቀናት በሳንኮ ኢንዱስትሪዎች በቀን ለ 7 ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ይሰራሉ፡፡

“ታማኪ ከጊነስ ባለስልጣናት የምስክር ወረቀታቸው እንደተቀበሉ እኔ ያረኩት ለ90 አመታት ማድርግ የሚጠበቅብኝ ብቻ ነበር ፤ ስለሆነም ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም…በጣም ደስ ብሎኛል” ብለዋል።

ታማኪ በኩባንያ እንዲህ አይነቱ ረጅም የስራ ሰአት ማሳካት ከተፈጥሮ የመነጨ ነው ሲሉ በሰአቱ የነበሩ የጊነስ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

እኔ የተወለድኩት ሰዎችን ለማገዝ እንደሆነ ነው ሁሉ ጊዜም የማስበው ፤ ስለዚህ ዋና ስራ አስኪያጅን እና ሊሎች የድርጅቱ ሰራተኞች የሚያስድስታቸው ነገር መስራት ፈልጋለሁ” ነው ያሉት። ታማኪ አሁን የእድሜ ልክ ገቢን ማሳካት ይቀረኛል ሲሉም ተደምጠዋል።

የኩባንያው ጽ/ቤት ሃላፊም አሁንም ቢሆን ጥሮታ ለመውጣት እቅድ የላቸውም ሲሉ ተናግረዋል። የ90 አመት የእድሜ ባለፀጋ ስራ አስኪያጅም ከእዚህ በኋላም ቢሆን በእንደዚ ሁኔታ ስራ ለመቀጠል እቅድ አለኝ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 02 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ