ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ በጅቡቲ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለ5ኛ ጊዜ አሸነፉ

0
318

ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ በጅቡቲ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለ5ኛ ጊዜ ማሸነፋቸው ተነግሯል።

የሀገሪቱ መንግስት ጊዜያዊ የምርጫ ውጤትን መሰረት በማድረግ ነው ፕሬዘዳንት እስማኤል ኦማር ጉሌህ ለ5ኛ ዙር ማሸነፋቸውን ያስታወቀው።

ፕሬዘዳንት እስማኤል ኦማር ጉሌህ በትናትናው እለት በተካሄደው ምርጫ ከተሰጠው 177 ሺህ 391 ድምፅ ውስጥ 98 በመቶ በማግኘት ማሸነፋቸው በጊዜያዊ የምርጫ ውጤቱ ተመላክቷል።

ፕሬዘዳንት እስማኤል ኦማር ጉሌህ በትዊተር ገጻቸው “በእኔ ላይ ስላሳያችሁት መተማመን አመሰግናለሁ”፤ “በቀጣይም አብረን እንጓዝ” ብለዋል።

የፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ሙሉ ውጤት ዛሬ ከሰዓት ላይ ይፋ እንደሚያደረግም አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ፕሬዘዳንት እስማኤል ኦማር ጉሌህ ላለፉት 22 ዓመታት በስልጣን ላይ መቀጠላቸው ሳያንስ ለተጨማሪ ዓመታት ለመምራት በምርጫው መወዳደራቸው ፓርቲዎች መቃወማቸው ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ከአንድ ፓርቲ በስተቀር ሌሎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምርጫው አስቀድመው ራሳቸውን አግልለዋል።

የቀድሞው ወታደር እና አሁን ላይ በንግድ ስራ የሚተዳደሩት ዘከሪያ እስማኤል ፋራህ ብቸኛው በምርጫው የተሳተፉ ተቃዋሚ ፓርቲ ነበሩ።

አንድ ሚሊየን የማይሞላ ህዝብ ብዛት ያላት ጅቡቲ ከጠቅላላ ሀዝቧ 14 በመቶዎቹ ስር በሰደደ ድህነት ውስጥ እንደሚኖሩ የዓለም ባንክ መረጃ ያስረዳል።

ጅቡቲ ካላት ተፈጥሯዊ ቦታ አንጻር የበርካታ የዓለማችን ሀያላን ሀገራት ወታደራዊ ማዘዣዎቻቸውን ገንብተዋል።

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 02 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ