ቢፈነዳ አዲስ አበባን በሙሉ ማውደም የሚችል አቅም ያለው ኬሚካል ሳይወገድ አለ ተባለ

0
210

በአዲስ አበባ የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበት እስከ 250 ኪ/ሜ ርቀት ድረስ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል የኬሚካል ክምችት አለ ተባለ።

የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃጂ ኢብሳ ኬሚካሉ ቢፈነዳ አዲስ አበባን በሙሉ ማውደም የሚችል አቅም አለው ብለዋል፡፡

ለዘመናት ሳይወገዱ ተከማችተው የቆዩ የተለያዩ ዓይነት የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው ኬሚካሎች በየመጋዘኑ እንደሚገኙ የተናገሩት ዳይሬክተሩ ኬሚካሎቹን ለማስወገድ ከምሁራን ጋር በመተባበር ጥናት ተጀምሯል ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ሐጂ ኢብሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በአዲስ አበባ ላፍቶ አካባቢ በሚገኝ አንድ መጋዘን የተጠራቀመው የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበት ኬሚካል ብቻ ቢፈነዳ አዲስ አበባን በሙሉ ማውደም የሚችል አቅም አለው ብለዋል፡፡250 ኪ/ሜ ራዲየስ ዙሪያ ያለን ቦታ ሁሉ ማጥፋት ይችላል የተባለው ይህ ኬሚካል ለምን ዓላማ ወደ ሃገር የገባ እንደሆነ አልተናገሩም።

የኬሚካሎችን ክምችት ለማስወገድ እንዲቻል ኤጀንሲውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁራን ተባብረውት በተለያየ መስክ በበጎ ፈቃድ ጥናት ማድረግ ጀምረዋል ተብሏል፡፡

ምሁራኑ ለግብርና ተብለው የገቡ ኬሚካሎች፣ የኢንዱስትሪ ኬሚካሎችንና የኤሌክትሮኒክስ ኬሚካሎችን ክምችት ለየብቻ ለማጥፋት 3 ኮሚቴዎች ተዋቅረው ስራ መጀመራቸውን ሰምተናል።

ለማስወገድ የሚያግዝ ገንዘብም ከለጋሾች እየተፈለገ መሆኑን አቶ ሃጂ ተናግረዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኬሚካሎችን ጨምሮ ሌሎች በየፌዴራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች ያለን ሀብት ለመመዝገብ የሚጠቅምና የማይጠቅመውን ለመለየትም ስራ ተጀምሯል ተብሏል፡፡

በመሆኑም ጊዜ ካለፈባቸው ኬሚካሎች ባሻገር ያለአገልግሎት በየመስሪያ ቤቱ የተከማቹ የቢሮ መገልገያ እቃና ተሽከርካሪዎች ለይቶ በሽያጭ ለማስወገድ እንደታሰብም አቶ ሐጂ በመግለጫው ተናግረዋል በማለት የዘገበው ሸገር ሬዳዮ ነው፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 02 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ