በወልድባ የገዳም አባቶች ላይ ምንድነው የተፈጠረው?

0
588

በማንነታቸዉ ምክንያት የዋልድባ ገዳምን “ለቀን እንድነወጣ ተደርገናል” መነኩሴዎች አዉሎ ሚድያ አሁን ያሉበት ሁኔታ ጠይቋል፡፡

ከ 500 በላይ የትግራይ ተወላጅ መነኩሴዎች ለአመታት ከኖሩበት የዋልድባ ገደም በብሄራቸዉ ምክንያት ጥቃት እንደደረሰባቸዉ ነዉ የሰማነዉ፡፡

አዉሎ ሚድያ የተፈናቀሉ መነኩሳትን በስልክ አግኝቶ አናጋግሯል፡፡ መጋቢት 5ቀን 2013 ዓ.ም እንደወትሮዉ በቤተክርስትያን ቅዳሲያቸዉን አሰቀድሰዉ ወደ መኖሪያቸዉ ተመልሰዉ እንዲሁም የሚበላ ይዘዉ አራት ሰአት አካበቢ ወደ ቤተክርስትያን ሲመለሱ ቤተክርስትያኑን እንደተዘጋባቸው ነገሩን፡፡

“በዛ ሰአት ለሚመለከተዉ የማይ ጸብሪ ከተማ ወረዳ ጸለምቲ ጽህፈት ቤት አሳዉቀን ለዘጉት አካላት በስልክ አናግረዋቸዉ በቃ ሂዱ እናስከፍተዋለን የሚል መልስ ተሰጠን” ሲሉ ይናገራሉ፡

ይሁን እንጂ በሚቀጥለዉም ቀን ስላልተከፈተ የዘጉት አካላት እንዲከፍቱልን ስንጠይቃቸዉ ልናስከፍትላችሁ ይቅርና ከዚህ መኖሪያና ገዳም ለቃችሁ እንድትሄዱ ነዉ የምንፈልገዉ እንደተባሉ ነገሩን፡፡

አሁንም ቅሬታችንን ያቀረብንበት ጽህፈት ቤት በድጋሜ ስንሄድ  አንከፍትም እንዳሏችሁ ማረጋገጥ አለብን የሚል መልስ አገኙ፡፡እንደዚህ ሆኖ እያለ መጋቢት 12 ቀን ላይ በመነኩሴዎች አይዞህ ባይነት የአካባቢዉ ኗሪዎች ገዳሙ ድረስ መጥተዉ  ወጣቶችንና በ90ዎቹ እድሜ ክልል የሚገኙ መነኩሴዎች ሳይቀር መደብደባቸዉን በገዳሙ ለ 11 አመታት የቆዩትና የጥቃቱ ሰለባ የሆኑትን መነኩሴ ነግረዉናል፡፡

እነዚህ ለረጅም አመታት በዋልድባ ገዳም ተጠልለዉ ሲያገለግሉ የነበሩት ከ500 በላይ የሚሆኑ መነኩሴዎች በማንነታቸዉ ምክንያት ከገዳሙ ተፈናቅለዉ በጸለምቲና ሽረ እንዳስላሰ በሚገኘዉ ቤተ ክርስትያን ተጠልለዉ እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል፡፡

ይህንን ጉዳይ በመያዝ የተፈናቀሉት መነኩሴዎችን በተመለከተ ሊደረግ የሚችለዉን ድጋፍና ወደ ገዳሙ የሚመለሱበት ሁኔታ ካለም እስካሁን የተሰራ ስራ ይኖር ይሆን በማለት ወደ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የገዳማት አስተዳደር መምርያ ጽኅፈት ቤት መልስ እንዲሰጡን ደዉለናል፡፡

የመምሪያዉ ዋና ጸሀፊ መ/ር ሱራፍኤል ተፈራ ግን መነኩሴዎቹ ጋር ስለደረሰ እንግልት ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸዉና ለመጀመሪያ ጊዜ ከሚድያችን እየሰሙት እንዳለ ነዉ የነገሩን፡፡ አሁንም አውሎ ይህንን ጉዳይ ተከታትሎ የሚኖሩ አዲስ መረጃዎች ወደ እናንተ ያደርሳል፡፡

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 02 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ